Skip to main content

ሳላሀዲን ሰዓድ ካዋራኝ የተገለበጠ ኢንተርቪው

Invisible journalist asking question through Magnetic Force of the mind

First Audition

የእምነት ነፃነት መፅሄት የመጀመሪያው እትም በሆነው ቅፅ ፻ የእንግዳችን ፕሮግራም አምድ ላይ ተጋባዥ ያደረግነው የጭንቅ ቀን ደራሹ የብሄራዊ ቡድናችን አጥቂ ከሆነው ሳላሀዲን ሰዒድ ጋር ያደረግነውን አጭር ቆይታ እነሆ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡

የእምነት ነፃነት መፅሄት፡ ሳላሀዲን መቼም በዚህ አጭር ግዜ ውስጥ (ልምምድ ላይ እንደመሆንህ መጠን) ለቃለ ምልልሱ ፍቃደኛ ሆነህ ስለመጣህ እያመሰገንን በቅድሚያ በአንባቢዎቻችን ስም እንኳን በደህና መጣህ ለማለት እንወዳለን፡፡

ሳላሀዲን እንኳን ደህና ቆያችሁኝ፣ የመጀመርያ እንግዳም ስላደረጋችሁኝ አመሰግናለሁ፡፡

ጥያቄ፡ ሙስሊም እንደመሆንህ መጠን የመጅሊስ ምርጫ በቀበሌ መባሉን እንዴት ነበር ያየህው?

ሳላሀዲን፡ በግልምጫ፡፡

ጥያቄ፡ ለምን?

ሳላሀዲን፡ ምክንያቱም ድርጊቱ በመረብ ኳስ ሜዳ ላይ ጎል ተክሎ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያን የመጫወት ያህል ነው፡፡

ጥያቄ፡ የመንግስት አካላት ምርጫው በቀበሌ መሆኑ ህገመንግስቱን አይፃረንም ባዮች ናቸው አንተ ምን ትላለህ?

ሳላሀዲን፡ እግር ኳስ ተጫዋች ስለሆንኩ የመረዳት አቅም የለውም በእግር ማሰብ አይደለም እንደማትለኝ እያመንኩ፡፡ ይህ ቀላል ጥያቄ ነው በሚቀጥለው ምርጫ 2007 የመንግስት ተወካይን ለመምረጥ የሀገሪቱ ህዝብ በመስጊድ እና በቤተክርስታን ማከናወን እንደሚችል ቃል ከገቡና በምርጫ ቦርድ ወይም በፓርላማው እንደ አንድ ፖሊሲ ካፀደቁት ምንም ችግር የለውም ባይ ነኝ፡፡

ጥያቄ፡ በሌላ መንገድ እምነት እና ፖለቲካን (ሰርግና ሞት አንድ ነው ጨፍር ምንድነው) እንደሚለው የሀገራችን ቢሂል ካደረጉት እንደማለት ነው?

ሳላሀዲን፡ አግኝተህኛል (ፈገግታ.. )

ጥያቄ፡ እንዴት ነው ህዝቡ እንደምታውቀው በሰላማዊ መልኩ ተቃውሞውን ላለፉት 11 ወራት ሲያካሂድ ነበር እንዴት ነው አንተስ ድምፅህን የምታሰማበትን አጋጣሚ ነበረህ?

ሳላሀዲን፡ በእርግጥ እንደዛ አይነት አጋጣሚን አላገኘሁም ብዙን ግዜ ጌሞች ስለሚደራረቡብን እና ከካንፕ የምንንቀሳቀስበት ግዜ በትሬኒንግ የተጨናነቀ እንደመሆኑ መጠን ምንም አላገኘሁም፡፡ ነገር ግን በውስጤ ሁሌም እፀልያለሁ፡፡

ጥያቄ፡ እንደ አንደ የሀገራችን የእምነቱ ተከታይ ብሎም ታዋቂ እንደመሆንህ መጠን ተቃውሞህን ለማሰማት ያሰብከው ነገር አለ?

ሰላሀዲን፡ ጥሩ ጥያቄ ነው የጠየቅከኝ፡፡ በእርግጥ ቀደም ብዬ ለመጥቀስ እንደሞከርኩት ብዙ አይነት የመቃወሚያ መንገድ እንደመኖሩ መጠን እኔ እስካሁን ሳደርገው የነበረው ፀሎት ወይም ዱዓን ነበር፡፡ ፈጣሪ ከተበዳዮች ጎራ እንደሚቆም አልጠራጠርም፡፡

ጥያቄ፡ ሌላ ለማድረግ የፈለግከው ነገር እንዳለ ከጓደኞችህ ሰምቻለው፡፡ ተቃውሞህን ለማሰማት ወሳኙ በሆነው በነገው ጫወታ ላይ፣ በሱዳን አቻችሁ ላይ ጎል እንዴት ነው አላስቆጥርም ብለህ ነበር እንዴ?

ሰላሀዲን፡ በፍፁም! በፍፁም! ይሄ የአንዳንድ ካድሬ የቤህራዊ ብድናችን ተጫዋቾች አስተሳሰብ ነው፡፡ አንተም ሆንክ እነሱ ግን ለመስማት ከፈለክ፣ እኔ እንደ ማንኛውም ሙስሊም የሀገርን ህልውና እና ሠላምን በማይረብሽ ብሎም እንዲሁም ልክ እንደ ሌሎች የሀገሬ ሙስሊም ወጣቶች ተቃውሞ ኮሽታን በማያሰማ አካልን ሳይሆን ልብ ያለው እእምሮ ላለው ጨቋኝነን በሚቆረቁር መንገድ ነው የማሰማው፡፡ እንደወትሮው ከቻልኩኝ ከአንድም ሶስት ጎሎችን በማስቆጠር ጥረት አድርጌ ባገባሁ ቁጥር ሀዘኔን እና የሙስሊሙ ጉዳይ እኔንም እንደ አንድ ሙስሊም የሚያሳስበኝ እንደሆነ ለመግለፅ፡፡ አግብቼ የማልፈነድቅ ወይም የማልሮጥ ሲሆን ወደ መሬት ሱዱጅ በመውረድ ተቃውሞዬን የምገልፅ ይሆናል፡፡ ይሄው ነው፡፡

ጥያቄ፡ መልካሙን ሁላ እየተመኘንልህ በመጨረሻ የምታስተላልፈው መልዕክት ካለህ እድሉን ልስጥህ፡፡

ሳላሀዲን፡ አመሰግናለሁ ድል ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድናችን፣ አፋጣኝ ምላሽ ከመንግስት ለእምነት ነፃነት ጥያቄያ ድምፃችን ይመጣ ዘንድ ምኞቴ እና መልዕኬቴ ነው፡፡
My own art to tell you the point
ከጫወታው አንድ ቀን በፊት
›››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››በህልሜ ካዋራኝ የተወሰደ‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹

Comments

  1. mashallah selhadin betam netuh sew. sew malet balbet bota bemichelew menged teqwmowen yegltal betam tekekel neh.allah kante gar yehun .hulum ethiopiawi kehulum belay feqer endmiyashenef yaweqal mengest gen lemen ? ethiopiawi aydelem ende ?

    ReplyDelete
    Replies
    1. Hey actually it is a dream of my own how ever I hope people like him may feel it like feel for him
      thanks for your comment any ways

      Delete
  2. Helmehen enten hedena asefetaw ok ga . . . t ! ! !

    ReplyDelete
  3. thanks አኒቲ that is such a cool Dream........

    ReplyDelete
  4. ወንድሜ (ጠያቂ ሆነ መላሲ)ጨወታ ና ሀይማኖት ለይ

    ReplyDelete
  5. This comment has been removed by a blog administrator.

    ReplyDelete

Post a Comment

Popular posts from this blog

The Historic Chaltu Speeks Out

Let me paint you the picture of what happened in ATL yesterday. Me and Riyad S abona walking, minding our own business and we see an anti-Jawar protest happening 200 yards away from the meeting entrance. The police directed us to walk in closer to the side of the protest to avoid obstructing traffic.  So we saw their flags and I decided to take out my Oromo flag and walk.  First, it was just the slurs, calling me Galla. Then it was the spit, in front and behind me and then one made it with the perfect aim to hit my cheek. I continued to walk with my head high with the utmost respect until one 'balance' thought it would be okay to reach over and snatch my flag. He thought he got the flag, but I killed that dream, but as soon as he reached again and grabbed my hijab, I turned around and his face hit the back of my hand (like how words can change everything?). Lol, I actually slapped the hell out of him. When I looked back they were grabbing on Riyad's trad...

ከዶ/ር መረራ አስለቃሽ ጭስ አንዷ

ዶር መረራ ጉዲናን ሁላችንም እንደምናውቃቸው፣ በሀገራችን የመማር ማስተማር እና የፖለቲካ ምህዳር እንደ አስተማሪም እንደ አማራሪም በመሆን ከፍተኛ ሚና የተጫወቱና አንቱታን ያተረፉ የሀገራችን ዜጋ ናቸው።  አንደበተ ርቱ ባይባሉም መናገር የፈለጉትን ነገር ከመናገር ወደኋላ የማይሉ፣ ንግግራቸው ግልፅ እና ግልብ ከሚባል ተርታ ይመደባል ባይ ነኝ። እሳቸው ተናግረው አልያም ተከራክረው ፈገግ ያላልኩበት አጋጣሚ ትዝ አይለኝም። ከሰሞኑን የመታሰራቸውን ነገር በሰማሁ ወቅት፣ አንደ ወዳጄ አቀልድ ማህደሩ ይሁን አዚዓ ማህደር እነወጃ፣ አሉ ብሎ ካካፈለኝ ፈገግ የምታሰኝ ንግግራቸውን ላካፍላቹ ወደድኩ። ነገሩ የሆነው ፓርላማ ሳሉ ነው አሉ። የወቅቱ አፈጉባኤ ደግሞ ክቡር አቶ ተሸመ ቶጋ ነበሩ። አናም የመናገር እድሉ ሲደርሳቸው አቶ ተሾመ፣ ባላቸው ማይኩን የመዝጋትና የመክፈት ስልጣን፣ ቀጥል ብለዉት ደር መራራን እንዲናገሩ ፈቀዱላቸው። እናሎ ታድያ ወቅቱ የፓርላማው አመታዊ ሪፖርት በጠቅላይ ሚንስትሩ የሚቀርብበት ነበር፣ እንደሚታወቀው ዶር መረራ ቡዙን ግዜ ፓርላማ ላይ የማይቀሩበት አጋጣሚ ይህ እንደሆነ ይታወሳል። ይህንንም አጋጣሚ በመጠቀም (ቢቆራረጥም) ሚዲያውን በአግባቡ ይጠቀማሉ። ዶር መረራ ጀመሩ ፦ "ሲለ ተሰጠኝ እድል ባመሰጊን፣ ‘ፉት ሲሏት ጭልጥ’ እንደሚለው ተረት ቲሆናለች እና የተሰጠን ሰዐት ኢሀዴግ…" ብለው ሳይጨርሱ፣ አፈጉናኤው እላያቸው ላይ ማይኩን ጥርቅም አድርጉት። አፈ ጉባኤው:– "ደ/ር መረራ ሌላ ሌላውን ይተውና አጊባብነት የለው ጥያቄ ያቅርቡ፣ ጥያቄዎት ወይም አስታየቶ ክብር ሚኒስትሩ ባቀረቡት ሪፖርት ላይ ብቻ ይሁን፣ ከተሰጦት ሰዓት 5 ደቂቃ ብቻ ይቀሮታል" ቁጣን ባለው ለዛ ብለው  እንዳበቁ...

የድንቅነሽ/ሉሲ በደህና የመመለሷ ነገር . . .

ዛሬ ድንገት ኢቲቪ ተከፍቶ ዜና ሠማሁኝ እና ከዜናው አንዱ ትኩረቴን ሳብ አድርጎት ጆሮዬን ቀልቤን አቅሌን ሙሉ ለሙሉ ለኢቲቪ ሰጠሁ፡፡ ታድያሎ ያልኳችሁ ዜና እናንተም የሰማችሁት ያ ስለ ድንቅነሽ /ሉሲ/ ከ5 ዓመት ቆይታ ቡሀላ ከወደ አሜሪካን ሀገር ተመለሰች የሚለው ነበር፡፡ ገና የዜናው ርዕስ እንደሰማሁኝ ነበር፤ እንኳን በደህና ሄደሽ ባልልም፤ እንኳን ደህና መጣሽ ማለቴ ግድ ነበር፤   እናም አልኩኝ፡፡ ሙሉ የዜናውን ሀተታ እና የምስል ቅንብር ስመለከት፤ለርክክቡም አሜሪካዊ እና ታዋቂ ብሎም አዋቂ የኢትዮጰያዊ ተመራማሪዎች ከአሜሪካን ድረስ እዚህ መገኘታቸውን ሠማሁ፡፡ ከዛማ እንኳን በደህና ተመለስሽ ያልኩት አባባል ግልፅነት እና ተጠያቂነት የጎደለው ደብዛዛ ምስክርነት መስሎ ታየኝ፤ ጥርጣሬም ወረረኝ፡፡ ለምን እና እንዴት ካላችሁ. . . . . የ እኛ ምሁራን ሉሲን ገቢ ያደረጉበት የማረጋገጫ መለኪያ ተጠቀምን ያሉት ስልት እንደ ስለት አሳቀቀኝ፡፡ ፕሮፌሰሩ ቃል ሲሰጡ፤ “እያንዳንዷን አጥንት መዝነን፣ ለክተን ነው የተቀበልነው::” በዜናው ላይ የቀረበው የ ርክክብ ቪዲዮ ላይ እንዳየነው፤  እና መገለጫችን የሆነውን የሉሲን አፅም ለዛውም ለ5 ዓመት ያህል ሠው ቤት ቆይቶ እንደሚመለስ ብርቅዬ ቁስ ሳይሆን እንደ አሞሌ ሲቀባበሉ መመልከቴ አስገርሞኛል፡፡ በተለይ በተለይ የእኛው ምሁራን ይህችን በስንት ምርምር የእድሜ ጠገብነቷን ሚስጢር በዓለም አቀፍ ደረጃ ለመለየት ብዙ ምርምር የተደረገላትን በክብደት እና ቁመት በመለካት ማረጋገጥ ችለናል ማለታቸው አግራሞት ፈጥሮብኛል፡፡ እኔ የምለው እንደው ደረጃ መዳቢዎች ባለስልጣን እራሱ ዘይትን ከውጪ ለማስገባት ምን ያህል የላብራቶሪ ፍተሸ እናደሚያካሂድ ባለፈው ዘይት እንትን ያ...