ዛሬ ድንገት ኢቲቪ ተከፍቶ ዜና ሠማሁኝ እና
ከዜናው አንዱ ትኩረቴን ሳብ አድርጎት ጆሮዬን ቀልቤን አቅሌን ሙሉ ለሙሉ ለኢቲቪ ሰጠሁ፡፡ ታድያሎ ያልኳችሁ ዜና እናንተም
የሰማችሁት ያ ስለ ድንቅነሽ /ሉሲ/ ከ5 ዓመት ቆይታ ቡሀላ ከወደ አሜሪካን ሀገር ተመለሰች የሚለው ነበር፡፡ ገና የዜናው ርዕስ
እንደሰማሁኝ ነበር፤ እንኳን በደህና ሄደሽ ባልልም፤ እንኳን ደህና መጣሽ ማለቴ ግድ ነበር፤ እናም አልኩኝ፡፡
ሙሉ የዜናውን ሀተታ እና የምስል ቅንብር
ስመለከት፤ለርክክቡም አሜሪካዊ እና ታዋቂ ብሎም አዋቂ የኢትዮጰያዊ ተመራማሪዎች ከአሜሪካን ድረስ እዚህ መገኘታቸውን ሠማሁ፡፡ ከዛማ
እንኳን በደህና ተመለስሽ ያልኩት አባባል ግልፅነት እና ተጠያቂነት የጎደለው ደብዛዛ ምስክርነት መስሎ ታየኝ፤ ጥርጣሬም
ወረረኝ፡፡
ለምን እና እንዴት ካላችሁ. . . . .
የእኛ ምሁራን ሉሲን ገቢ ያደረጉበት የማረጋገጫ መለኪያ ተጠቀምን ያሉት ስልት እንደ ስለት
አሳቀቀኝ፡፡ ፕሮፌሰሩ ቃል ሲሰጡ፤ “እያንዳንዷን አጥንት መዝነን፣ ለክተን ነው የተቀበልነው::”
በዜናው ላይ የቀረበው የርክክብ ቪዲዮ ላይ እንዳየነው፤ እና መገለጫችን የሆነውን የሉሲን አፅም ለዛውም ለ5 ዓመት ያህል ሠው ቤት
ቆይቶ እንደሚመለስ ብርቅዬ ቁስ ሳይሆን እንደ አሞሌ ሲቀባበሉ መመልከቴ አስገርሞኛል፡፡
በተለይ በተለይ የእኛው ምሁራን ይህችን በስንት ምርምር የእድሜ ጠገብነቷን ሚስጢር በዓለም አቀፍ ደረጃ
ለመለየት ብዙ ምርምር የተደረገላትን በክብደት እና ቁመት በመለካት ማረጋገጥ ችለናል ማለታቸው አግራሞት ፈጥሮብኛል፡፡ እኔ
የምለው እንደው ደረጃ መዳቢዎች ባለስልጣን እራሱ ዘይትን ከውጪ ለማስገባት ምን ያህል የላብራቶሪ ፍተሸ እናደሚያካሂድ ባለፈው
ዘይት እንትን ያለ ሠሞን ያየነው ላብራቶሪ ምስክር ነው፡፡ እናሳ ምነው ለሉሲሳ አስብሎኛል፡፡
ምን ትዝ እንዳለኝ ታውቃላችሁ፣ ጣሊያናዊ ማፍያዎች ከትልልቅ ሙዚየሞች እድሜ ጠገብ እና ብርቅዬ የታዋቂ
ሠዎችን ኦርጅናል የስእል ስራዎች ለመስረቅ አስመስለው የሚሰሩት ጥናታዊ የዘረፋ እና የመሸሸግያ (እራሳቸው የሙዝየም አስተዳደሮች
ሌላ አመሳስለው በመስቀል እንዳይዘረፍ) የሚያደርጉትን ነገር ከተለያዩ ፊልሞች እና መፅሀፍቶች ያየኋቸው እና ያነበብኳቸው
ትርኢቶች እና ትሪኮች በአእምሮዬ ውስጥ ብልጭ ብልጭ እያሉ ጥርጣሬዬን አጠናከሩት፡፡
በመጨረሻም ወደገደለው ልግባና፡፡ ለእነኚህ
ሠዎች ለድፍን 5 ዓመት እቃ አውሶ በየዋህነት ምንም ጥቅም ሳያገኙበት እንደ ፎቶ ለህዝባቸው አሳይተው ብቻ ይመልሳሉ የሚል
እምነት በፍፁም የለኝም፡፡ እርግጠኛ ነኝ በሚያደርጉት የትኛውም ዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲያው ግንኙነት ምን ያክል ጥቅም አሳዳጆች
እንደሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ “National Interest” ብለው አይደል የሚያቆላምጡት እናሳ ለእኛስ ምን ነበረው፡፡
ብቻ የሆነው ሆኖ እኔ እንደ አንድ ዜጋ የተሰማኝ
ይሄ ነው፡፡
እናንተስ ዜናውን አይታችሁ ከሆነ ምን
ተሠማችሁ?
Comments
Post a Comment