Skip to main content

Posts

Showing posts from June, 2013

በብሄራዊ ቡድኑ መቀጣት የተነሣ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ባጃጆች የሥራ ማቆም አድማ ሊያደርጉ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ከደቡብ አፍሪቃ ባስመዘገበችው የዓለም ዋንጫ ማጣርያ ማሸነፍ ምክንያት ህዝቡ ሲያደርገው በነበርው ሀገር አቀፍ የፈንጠዝያ ዱብእዳ በተለያዩ የሀገሪቷ ትልልቅ ከተሞች (ማለትም መቀሌ፤ ባሕር ዳር፤ አዳማ፤ ሐዋሳ እና ሌሎችም) ውስጥ የሚኖሮ፣ ህንድ ሠራሽ ኢትዮጵያ ነዳሽ ባጃጆች ላያ ይህ ነው የማይባል የሰብዓዊ መብት ረገጣ በማከናወናቸው ምክንያት፣ በዛሬው እለት ባጃጆቹ ተወካዮቻቸውን መርጠው አዲስ አበባ ወደሚገኘው የህንድ ኢንባሲ መላካቸው ተገለፀ፡፡ የውስጥ ምንጮች ለዜና አውታራችን እንዳስረዱት ከሆነ፣ ጉዳዩን እስከዛሬ ችላ ብለው የቆዩት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እውነትም ለማጣሪያው አንድ ቀሪ ጫወታ እያለው በቀጥታ ማለፉን በመስማታችን እና በመስማማታችን ነው፣ ሲሉ ነገር ግን ለዛሬው አቤቱታ ያበቃቸውን ነገር ከመቀሌ የተመረጡት ህንድ ሠራሽ ሀበሻ ነዳሽ ታርጋ ቁጥራቸው  ኮድ 1   መ ቀ- 2334  የሆነው ባጃጅ እንዳሉት፤ “ሁለት ምክንያት  ለዚህ አቤቱታ እዚህ አዲስ አበባ ወደሚገኘው ሀገራችን የህንድ ኢንባሲ አምጥቶናል:: አንደኛው ነገር እኛ ለዚህች ሀገር እንሥራ እንጂ ዜጋዋ አይደለንም፣ ዜጋዋ ብንሆን ኖሮ እንዲህ ያለ ከፍተኛ ጉዳት እና ከፍተኛ የሞራል ውድቀት በራሳችን ወገን አይደርስብንም ነበር፤ ሆኖም ግን በሠው ሀገር እንደመሆናችን እና በተገኘው ውጤት የምናገለግለው ህዝብ ምንም ቢረግጠንም ተደስቶ ማየታችን ጥሩ ሆኖ ሳለ እስከዛሬም ዝም ብለን ችለን ዛሬ ግን ነጥብ መቀነሱን በመስማታችን እኛም እንዲህ ላለ ከንቱ ጉስቁልና መዳረጋችን ስላሳዘነን ነው አቤት ለማለት የመጣነው”  በማለት የተሠማቸውን ሀዘን ድብልቅልቅ ባለ ስሜት ገልፀውልናል፡፡ በሌላ በኩል ከሐዋሳ ተወክለው የመጡትን ታ...

የፈጠራ ሥራ ውድድር ማስታወቅያ

የኢትዮጵያ የኬሚስት ባለሞያዎች ማህበር በሀገሪቷ እድገት ውስጥ ያለውን ሚና ከፍ ለማድረግ፤ እነደ መቋቋሙ መጠን አስካሁን ተጨባጫ የሆነ ተግባርን ሳያከናውን ቆይቷል፡፡  ሆኖም ግን ሀገራችን እያስመዘገበች ያለው እድገት፣ ተነሳሽነታችንን በእጅጉ እንደሚያነቃቃ በማመን፣ ማህበሩ ለውድድርነት ይሁን ዘንድ ይህንን የመወዳደሪያ ዘርፍ ለመጀመርያ ግዜ ማስለፈፍ አስፈልጓል፡፡ ተፈላጊ ችሎታ፡- በኬሚስትሪ ወይም በኬሚካል ኢንጂነሪንግ ከታወቀም ወይም ካልታወቀም ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ወይም የመጨረሻ  ዲግሪ ያለው ወይም ያላት፡፡ የመወዳደሪያ ዘርፍ፡- ሀገር በቀል አረቄ፡፡ የውድድሩ አስፈላጊነት፣ ግብ እና አላማ፡- የሚከተሉት አምስት ነጥቦች ለውድድሩ አስፈላጊነት እንዲሁም የትግበራው የረጅም እና የአጭር ግዜ ግብ እና አላማዎች ናቸው፣ 1.       በ ሀገራችን ያሉ ኬሚስቶችን በፈጠራ ሥራ ላይ ማበረታታት፡፡ 2.      የሀገራችን ኬሚስቶች፣ በሀገር እድገት ውስጥ፣ (ከማስተማር እና ከመማር ባሻግር) ሊኖራቸው የሚገባውን ተጨባጭ ሚና፣ ማጠናከር፡፡ 3.      በፎርሙላ ማጣት ሳቢያ፣ አረቄ አውጪ ባልቴቶች፣ ለረዠም ግዜ ለኪሳራ እና ለስነልቦና ችግር እንደመጋለጣቸው መጠን፣  እስታንዳርዱን የጠበቀ የአረቄ ፎርሙላ በማውጣት በሀገር እኮኖሚ ላይ እየደረሰ ያለውን ውድመት መታደግ፡፡ 4.      ለኢትዮጵያ አረቄ አውጪዎች እና ቸርቻሪዎች ማህበር፣ ሳይንሳዊ ድጎማ በመስጠት አትራፊነታቸውን ማጠናከር እና በሀገር ...

ሲፈቀሩ ሽሽት፤ ሳያፈቅሩ ትዳር!

ፍቅርዬ ናት ብዬ፣ ያለውል የያዝኳት የውል ያለሆነችን፣ እኔም ሚስቴ ምላት ባሌ የምትለኝ፣ የውል ባል ያልሆንኳት ለሚቆጠር ዓመት፣ ከልቤ ያኖርኳት እሷም የምትወደኝ፣ እኔም የምወዳት ሽምቅቅ ያደርጋታል፤ ‘ ትዳር! ’ ብዬ ስላት፡፡                             በፍቅር መንደሬ፣ ከትማ ምትወደኝ ‘ እንጋባ! ’ ስላት፣ በመስፈርት ሸብባኝ፤ ውስጤ ቦታ-የሌላት፣ መጣች ያልተመራች በሥራ አጋጣሚ፣ ሦስቴ ከኔው የዋለች፤ በዛች ተብሰልስዬ፣ ብቀርባት በስንዝር በአንዴ ሠልላ፣ የውስጤን ለትዳር ግዜ ሳታባክን፣ ምንም ሳትፈቀር ብላኝ እርፍ አለች፣ ቀለበት እንሠር ፍየል እዚ. . . አልኩኝ፣ ዙሩ በጣም ሲከር፡፡ ለእኔዋ የታየኝ፣ እንደ እንቦሳ ጥጆች ጠብታ እንደጠገበች፣ ጠግባ እየቦረቀች ሳታውቅ በፍንጠዛ፣ ከደጇ እንደራቀች መሮጡም ሲደክማት፣ ሲመሻሽ ታውቃለች፤ አቁማ መቦረቅ ፣ ርቃ ለመመለስ፣ ብታዘግም ወዲ አይኖር ሚቀመስ፣ እናቷ ታልባለች፣ ተገዳ በጋዲ፡፡ እንደው የሠው ነገር፣ እኔንም ጨምሮ በጋርዮሽ ሕይወት፣ ለመኖር ተባብሮ በራስ መውደድ ጠኔ፣ ውስጣችን ተቋጥሮ፤ ሞልቶ የማይሞላን፣ አሸን ሺህ ፍላጎት፣ ስንከተል ላንደርስ ለሠው ሠው ካልኖረ፣ የሚፈላለግ ልብ፤ ጎጆን መች ይቀልስ? እሱ እሱን ሳስበው. . . ሠው እንደ ጉንዳን ነው፣ ኋላውን አያይም፣ የፊቱን ያፈቅራል ለትዳር ላይሆነው፣ የፊቱም የፊቱን፣ ዱካ ይከተላል፤ ሲመሽ በመጣደፍ፣ እንደ...