ኢትዮጵያ ከደቡብ አፍሪቃ ባስመዘገበችው
የዓለም ዋንጫ ማጣርያ ማሸነፍ ምክንያት ህዝቡ ሲያደርገው በነበርው ሀገር አቀፍ የፈንጠዝያ ዱብእዳ በተለያዩ የሀገሪቷ ትልልቅ
ከተሞች (ማለትም መቀሌ፤ ባሕር ዳር፤ አዳማ፤ ሐዋሳ እና ሌሎችም) ውስጥ የሚኖሮ፣ ህንድ ሠራሽ ኢትዮጵያ ነዳሽ ባጃጆች ላያ ይህ
ነው የማይባል የሰብዓዊ መብት ረገጣ በማከናወናቸው ምክንያት፣ በዛሬው እለት ባጃጆቹ ተወካዮቻቸውን መርጠው አዲስ አበባ ወደሚገኘው
የህንድ ኢንባሲ መላካቸው ተገለፀ፡፡
የውስጥ ምንጮች ለዜና አውታራችን እንዳስረዱት
ከሆነ፣ ጉዳዩን እስከዛሬ ችላ ብለው የቆዩት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እውነትም ለማጣሪያው አንድ ቀሪ ጫወታ እያለው በቀጥታ ማለፉን
በመስማታችን እና በመስማማታችን ነው፣ ሲሉ ነገር ግን ለዛሬው አቤቱታ ያበቃቸውን ነገር ከመቀሌ የተመረጡት ህንድ ሠራሽ ሀበሻ
ነዳሽ ታርጋ ቁጥራቸው ኮድ 1 መቀ-2334 የሆነው ባጃጅ እንዳሉት፤
“ሁለት ምክንያት ለዚህ አቤቱታ እዚህ አዲስ አበባ ወደሚገኘው ሀገራችን የህንድ ኢንባሲ አምጥቶናል:: አንደኛው ነገር እኛ ለዚህች ሀገር እንሥራ እንጂ ዜጋዋ አይደለንም፣ ዜጋዋ ብንሆን ኖሮ እንዲህ ያለ ከፍተኛ ጉዳት እና ከፍተኛ የሞራል ውድቀት በራሳችን ወገን አይደርስብንም ነበር፤ ሆኖም ግን በሠው ሀገር እንደመሆናችን እና በተገኘው ውጤት የምናገለግለው ህዝብ ምንም ቢረግጠንም ተደስቶ ማየታችን ጥሩ ሆኖ ሳለ እስከዛሬም ዝም ብለን ችለን ዛሬ ግን ነጥብ መቀነሱን በመስማታችን እኛም እንዲህ ላለ ከንቱ ጉስቁልና መዳረጋችን ስላሳዘነን ነው አቤት ለማለት የመጣነው”
በማለት የተሠማቸውን ሀዘን ድብልቅልቅ
ባለ ስሜት ገልፀውልናል፡፡
በሌላ በኩል ከሐዋሳ ተወክለው የመጡትን ታርጋ ቁጥራቸው ኮድ 1 ሐዋ-3724 የሓዋሳ ተወካይ ባጃጅ የዛሬውን የአቤቱታ ምክንያት ስንጠይቃቸው . .
.
እኛ የሐዋሳ ከተማ ባጃጆች የመቀሌውን የወንድማችንን ሀሳብ ሙሉ ለሙሉ የምንጋራ ሲሆን በተጨማሪም፣ ኢንባሲያችን ያመጣን ነገር እንደ ባህርዳሩ የጃፓን መኪና ስቃይ በቃኝ ብለን እራሳችን አጥፍተን ሠዎችን የምናጠፋበት አእምሮም ሆነ ጉልበት የሌለን ሲሆን፣ እንደ ሀገር አቀፍ ደረጃ የደረሠብንን የጉልበትብዝበዛ ከግምት ውስጥ በማስገባት የሀገራችን የህድ ኢንባሲ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመነጋገር የካሳ ክፍያ እንዲጠይቅልን ሲሆን፡፡ ይህንን ካሳ የኢትዮጵያ መንግስት በዓባይ ግድብ ግንባታ ምክንያት ለመካስ እጅ እንደሚያጥረው እንረዳለን፡፡ ሆኖም ግን፣ ሶስት ነጥቡን በማስቀነስ ለበለጠ ቁጭት ህዝቡን የዳረገው እና እኛንም ለዚህ አቤቱታ የዳረገንን ግድብ የማያስገድብ፣ በሙስና የማይደበደብ፣ በመርሳት በሽታ የሚንገበገበውን፣ የሀገሪቱን የእግር ኳስ ፌዴረሬሽን እና አመራሮቹን በመቅጣት ካሳ እንዲያስከፍልልን ከወዲሁ ለማሳወቅ እንወዳለን” በማለት አስገንዝበዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ እኚህ ባጃጆች ዛሬ ቀኑን
ሙሉ ከህንዱ ባለሙሉ አንባሳደር ጋር ውይይት ካደረጉ ቡሃላ ማምሻውን በሂልተን ሆቴል ባለ 5 ነጥብ ቅድመ ሁኔታ ያለው ጋዜጣዊ
መግለጫ ያወጡ ሲሆን፣ እነኚህ ቅድመ ሁኔታዎች ተፈፃሚ ካልሆኑ፣ በቀጣይነት በሀገሪቱ ታላላቅ የክልል እና የዞን ከተማዎች ውስጥ
የሚገኙ ባጃጆች እራሳቸውን በማበላሸት ሥራ የማቆም አድም እንደሚያደርጉ አስጠንቅቀዋል፡፡ በአጭሩ ያስቀመጧቸው አንኳር ነጥቦች
እነደሚከተለው ቀርበዋል፤
1. የሚቀጥለውን የመጨረሻ ማጣሪያ ጫወታ ሀገሪቱ ካላለፈች እና የፌዴሬሽኑ ባለስልጣናት ካልተቀጡ፤
2. የመብት ጥያቄዎቻቸው በአስቸኳይ ካልተመለሱ፣
3. ለደረሰብን አደጋ ተመጣጣኝ ካሳ በተገቢው ሁኔታ ካልተከፈለን፣
4. የታሠሩ የነፃ ፕሬስ ጋዜጠኞችን በአስቸኳይ ካልተፈቱ፤
5. የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎችን ህገመንግስታዊ መብታቸውን በመስጠት እንዲፈቱ እና በነሱ ላይ የተሠራውን
የሀሠት ውንጀላ ሐረካት ፊልምን ኢቲቪ እንደ ፌዴሬሽኑ አምኖ በይፋ ይቅርታ ይጠይቅ፡፡
ለአኒቲ
ብሎግ ለተጠናቀረው ዝርዝር ቀልድ አዘል የሀሠት ቁምነገር ዘገባ ቁምላቸው
ለእውነት ነኝ መቀለ፡፡


Comments
Post a Comment