ዶር መረራ ጉዲናን ሁላችንም እንደምናውቃቸው፣ በሀገራችን የመማር ማስተማር እና የፖለቲካ ምህዳር እንደ አስተማሪም እንደ አማራሪም በመሆን ከፍተኛ ሚና የተጫወቱና አንቱታን ያተረፉ የሀገራችን ዜጋ ናቸው። አንደበተ ርቱ ባይባሉም መናገር የፈለጉትን ነገር ከመናገር ወደኋላ የማይሉ፣ ንግግራቸው ግልፅ እና ግልብ ከሚባል ተርታ ይመደባል ባይ ነኝ። እሳቸው ተናግረው አልያም ተከራክረው ፈገግ ያላልኩበት አጋጣሚ ትዝ አይለኝም። ከሰሞኑን የመታሰራቸውን ነገር በሰማሁ ወቅት፣ አንደ ወዳጄ አቀልድ ማህደሩ ይሁን አዚዓ ማህደር እነወጃ፣ አሉ ብሎ ካካፈለኝ ፈገግ የምታሰኝ ንግግራቸውን ላካፍላቹ ወደድኩ። ነገሩ የሆነው ፓርላማ ሳሉ ነው አሉ። የወቅቱ አፈጉባኤ ደግሞ ክቡር አቶ ተሸመ ቶጋ ነበሩ። አናም የመናገር እድሉ ሲደርሳቸው አቶ ተሾመ፣ ባላቸው ማይኩን የመዝጋትና የመክፈት ስልጣን፣ ቀጥል ብለዉት ደር መራራን እንዲናገሩ ፈቀዱላቸው። እናሎ ታድያ ወቅቱ የፓርላማው አመታዊ ሪፖርት በጠቅላይ ሚንስትሩ የሚቀርብበት ነበር፣ እንደሚታወቀው ዶር መረራ ቡዙን ግዜ ፓርላማ ላይ የማይቀሩበት አጋጣሚ ይህ እንደሆነ ይታወሳል። ይህንንም አጋጣሚ በመጠቀም (ቢቆራረጥም) ሚዲያውን በአግባቡ ይጠቀማሉ። ዶር መረራ ጀመሩ ፦ "ሲለ ተሰጠኝ እድል ባመሰጊን፣ ‘ፉት ሲሏት ጭልጥ’ እንደሚለው ተረት ቲሆናለች እና የተሰጠን ሰዐት ኢሀዴግ…" ብለው ሳይጨርሱ፣ አፈጉናኤው እላያቸው ላይ ማይኩን ጥርቅም አድርጉት። አፈ ጉባኤው:– "ደ/ር መረራ ሌላ ሌላውን ይተውና አጊባብነት የለው ጥያቄ ያቅርቡ፣ ጥያቄዎት ወይም አስታየቶ ክብር ሚኒስትሩ ባቀረቡት ሪፖርት ላይ ብቻ ይሁን፣ ከተሰጦት ሰዓት 5 ደቂቃ ብቻ ይቀሮታል" ቁጣን ባለው ለዛ ብለው እንዳበቁ...