Skip to main content

Posts

Showing posts from August, 2013

ስትሄጅ አትንገሪኝ

ምንም አትበይኝ፣ ስትሄጂ ጥለሺኝ ዝም ብለሽ ሂጂ፣ መሄድሽን ሳትነግሪኝ፤ ከኔጋር ለመሆን፣ ልብሽ ባይፈቅድልሽ መንገዱ ግን ይቅናሽ፣ ክፋም አይግጠምሽ፤ ፍቅርሽን መሸከም፣ ጫንቃዬ ባይችልም ከኔ ጋር ሁኚ፣ ብዬ አላስገዽሽም:: መሳቅ ሲያስፋልገኝ፣ በትዝታ አይሻለሁ ማልቀስ ቢያስፈልገኝ፣ ብቻዬን ቁጭብዬ እነፈርቃለሁ፤ በቃ በቃ ሂጂ፣ ዞር ብለሽ አትይኝ ሆዴን አታባቢው፣ ቻዎም አትበይኝ፤ ድምዕሽን አጥፊና፣ ኮቴሽን ጠብቀሽ ሳታንኮሻኩሺ፣ ውጪ ልቤን ዘግተሽ ቁልፉን ግን አስቀምጪው፣ አደራ ይሁንብሽ፡፡ ታዬ አለሙ 2005 ዓም ትንሽ ማስተካከያ ›› በአኒቲ

እናት - ያው - እናት - ናት!

በዚህ በኩል -  ህጉን ጣስሽ ብሎ፣ ያመናጭቃታል የደኑ ጥበቃ፣ ይተናኮላታል ፣   ሊያስር ያሳዳታል ሸክሟን ያስጥላታል፣ በባዶ ይሰዳታል ለእሷ ምግቧ ነው፣ ጉርሷ ይጨንቃታል፤ እውነት ለመናገር፣ አሷስ መቼ ጨንቋት ከእሷም ጉርስ በላይ፣ አለ ሚያሳስባት እንዲ አስጠግርሮ፣ ወገቧን ሚቆርጣት የሀረጓ ቅጣያ፣ የማህፀኗ ክፋይ ፣ የይሆናል እዠት መቼስ ገመተና? ይችል እንደሆነ፣ አንድ እንኳ ሊኖራት፤ ሲርበው የሚያለቅስ፣ ሲጠግብ የሚቧረቅ፣ ሄኔ ያስተኛችው ማንያውቃል ይኖራት ይሆናል፣ ባለማወቅ ብቻ፣ ብዙ የወለደቸው ተርቦ ሚገባ፣ ይማርልኝ ብላ፣ ትምህርት የላከቸው፡፡ ተሸክማ ደክማ፣ ጎብጣና ገርጥታ፣ ሆና ያልተሻለች ከዛሬ ህይወቷ፣ የተሸለ እንዲኖር፣ ለልጇ የተመኘች ፤ አመጣጡን ያውቃል፣ ጠንክሮ ይማራል ከግቡ ላይ ደርሶ፣ ላቤን ይጠርገዋል ፤ ምን ያደርጋል ታድያ፣ በሕልም ዓለም ስትስል ተጨናገፎ ቢቀር፣ የልቧን ሣያክል:: ዛሬን እንዳረጀች፣ የጇን መች አገኘች ህልሟ መች ተሳካ፣ መች ምኞቷን ኖረች ከአሁን ቡሀላ፣ መችስ ትኖራለች፤ ተስፋዬ ያለችው ገና ነፍሱን ሳያውቅ፣ ሱስ ቀድሞ እያወቀ ጠንክሮ እንደመስራት፣ በወሬ እየሞቀ፤ ላይብረሪ እያለ፣ ፑል-ቤት ሄዶ መዋል አዳር ላጥና ብሎ፣ በጭፈራው መጋል ከማይሆኑ ገጥሞ፣ እነሱን ለመምሠል፤ ልፋቷን በትኖት፣ ዋልጌ ሆኖ ቀረ፣ ገና በ ሀይ-እስኩል፡፡ ከወገቧ ጉብጠት፣ ከሸክሟም ክብደት ልቧ እንዳይሠበር፣ ሁሉም ፍቅር ይስጣት የኛ እናት ባትሆንም፣ በሠፈር ካወቅን፣ እንደዚህ ያለች ሴት ብቻዋን እንዳቱል፣ ሄደን እናጫውታት፣ ካለንም እንርዳት በዓልም ሲደርስ፣ እንሂድ እናፅናናት፣ እንደ ልጅ እንሁናት ቸ...