Skip to main content

Posts

Showing posts from July, 2013

እየኖሩ ሞት

ሠምተን ስትሠቃይ፣ ከነጎድን ትተናት እየቻልን ማቅናት፣ ከጎን ቆመንላት በግዴለሽነት፣ ረጋግጠን ካለፍናት ትርጉሟ በተግባር፣ መስጠት ከሌለባት መኖር ምን መኖር ናት? ለራስ እየበሉ፣ ሌላ ተርቦባት ለራስ ተጋጊጠው፣ ይሄ ታርዞባት ቤቤት ተጠልለው፣ ተርፎ እያከራ ዩ ት፤ በራስ መውደድ ጠኔ፣ በየቁም ድንዝዛት ሲያድር ሠው ትቦ ውስጥ፣ አይተው እንዳላዩት ሢያስል በክረምቱ፣ ሠምተው እንዳልሠማት:: እንኳን እና ገንዘብ፣ ወይን የቁስ ንብረት መች የማያስከፍል፣ የልብ ፍቅር ሠጡት ቆሻሻ እያረጉት፣ ነጣቂ  ነው አሉት ምክንያቱን ሳያያዩት፣ ቀርበው ሳይረዱት የአደም ልጅ መሆኑን፣ እያወቁ ሳቱት፡፡ መኖር ሳትሆን ይቺህ፣ የማይሠጥ ሠው ህይወት ያለምንም ለቅሶ፣ ያለአንዳች ግንዛት እየተነፈሱ እየተራመዱ፣ እያካበቱባት ሀፍት እየታዩ እያሉ፣ እየኖሩ ሞት ናት፡፡ ሐምኔ 15፣ 2005 © አኒቲ