Skip to main content

Posts

Showing posts from February, 2013

በህዳሴው ግድብ ስም አስገራሚ ማጭበርበር

ሰሞኑን የወዳጄ ወዳጅ ከምሽቱ ሦስት ሠዓት ተኩል አከባቢ አንድ የስልክ ጥሪ ያስተናግዳል፡፡  ከበስተማዶ ያለው ደዋይ ድምፅ ሆነ ንግግር ቅልጥ ካለ የአየር ላይ የሬዲዮን ውይይት ይመስላል፡፡ መሆኑም አልቀረ በጣም ብዙ ልምድ ያለው ጋዜጠኛ የሚመስለው ግለሰብ ጎርነን ባለ ድምፅ  ‹‹ከኤፍ ኤም ነው ጤና ይስጥልኝ›› ብሎ ሠላምታውን ያቀርብለታል፡፡ የወዳጄ ወዳጅ ከማያውቀው የስልክ ጥሪ ባገኘው ሞቅ ያለ ሠላምታ ድንግርግር እያለ ፈጣሪን በማመስገን ምላሹን በሠላምታ ሠጠው፡፡ ከስልኩ ወድያ ማዶ ያለው ጋዜጠኛው ደዋይ ቀጥሏል   ‹‹…….. ይህ አዲስ የሬድዮ ፕሮግራም ዜጎች ለህዳሴው ግድብ ግንባታ ያላቸውን ርብርብ በዘለቄታው ለማነሳሳት እና በግድቡ ዙርያ ያላቸውን እውቀት ለማጠናከር በማሰብ የተዘጋጀ ነው፡፡ ፕሮግራሙ በታዋቂው የሀገራችን ባለሀብት አቶ (እከሌ) ድርጅቶች አማካኝነት እስፖንሰር የተደረገ ሲሆን የተለያዩ የሀገራችን ዜጎች ስልክ ላይ በመደወል ስለ ህዳሴው ግድብ አስመልክቶ 3(ሶስት) ጥያቄዎችን የምንጠይቅ ሲሆን ለሶስቱም ጥያቄዎች ሙሉ ምላሽ ለመለሱ የ 5000 (አምስት ሺህ) ብር ሽልማት አቅራቢያው በሚገኝ ባንክ አማካኝነት በመላሹ ስም ወይም በአካውንት ቁጥሩ እናስተላልፋለን፡፡››  በማለት ጠቅላላ አላማውን እና ሂደቶቹን በአጭሩ አስቀመጠለት፡፡ እናላችሁ የወዳጄ ወዳጅ የሠማውን ማመን እያቃተው፣ አረንጓዴው የመቶ መቶ የብር ረብጣ በፊቱ ውልብ እያለ፣ እድለኛነቱን በውስጡ እያደነቀ፣ መጓጓቱን በሚያሳብቅ ድምፅ  ‹‹ … እሺ አመሰግናለሁ ጠይቁኝ … (መግደርደሩን ለመግለፅ እና መጓጓቱን ላለማሳወቅ) እሞክራለሁ›› በማለት ለኤፍ.ኤም. ጋዜጠኛ ነኝ ባዩ ደዋይ የንግግሩን ቀጣይነት የ...