ሰሞኑን የወዳጄ
ወዳጅ ከምሽቱ ሦስት ሠዓት ተኩል አከባቢ አንድ የስልክ ጥሪ ያስተናግዳል፡፡
ከበስተማዶ ያለው ደዋይ ድምፅ ሆነ ንግግር ቅልጥ
ካለ የአየር ላይ የሬዲዮን ውይይት ይመስላል፡፡ መሆኑም አልቀረ በጣም ብዙ ልምድ ያለው ጋዜጠኛ የሚመስለው ግለሰብ ጎርነን ባለ
ድምፅ
‹‹ከኤፍ ኤም ነው ጤና
ይስጥልኝ›› ብሎ ሠላምታውን ያቀርብለታል፡፡ የወዳጄ ወዳጅ ከማያውቀው የስልክ ጥሪ ባገኘው ሞቅ ያለ ሠላምታ ድንግርግር
እያለ ፈጣሪን በማመስገን ምላሹን በሠላምታ ሠጠው፡፡
ከስልኩ ወድያ ማዶ
ያለው ጋዜጠኛው ደዋይ ቀጥሏል
‹‹…….. ይህ አዲስ የሬድዮ
ፕሮግራም ዜጎች ለህዳሴው ግድብ ግንባታ ያላቸውን ርብርብ በዘለቄታው ለማነሳሳት እና በግድቡ ዙርያ ያላቸውን እውቀት ለማጠናከር
በማሰብ የተዘጋጀ ነው፡፡ ፕሮግራሙ በታዋቂው የሀገራችን ባለሀብት አቶ (እከሌ) ድርጅቶች አማካኝነት እስፖንሰር የተደረገ ሲሆን የተለያዩ
የሀገራችን ዜጎች ስልክ ላይ በመደወል ስለ ህዳሴው ግድብ አስመልክቶ 3(ሶስት) ጥያቄዎችን የምንጠይቅ ሲሆን ለሶስቱም ጥያቄዎች
ሙሉ ምላሽ ለመለሱ የ 5000 (አምስት ሺህ) ብር ሽልማት አቅራቢያው በሚገኝ ባንክ አማካኝነት በመላሹ ስም ወይም በአካውንት
ቁጥሩ እናስተላልፋለን፡፡››
በማለት ጠቅላላ አላማውን እና ሂደቶቹን በአጭሩ አስቀመጠለት፡፡
እናላችሁ የወዳጄ ወዳጅ
የሠማውን ማመን እያቃተው፣ አረንጓዴው የመቶ መቶ የብር ረብጣ በፊቱ ውልብ እያለ፣ እድለኛነቱን በውስጡ እያደነቀ፣ መጓጓቱን በሚያሳብቅ
ድምፅ
‹‹ … እሺ አመሰግናለሁ ጠይቁኝ … (መግደርደሩን ለመግለፅ እና
መጓጓቱን ላለማሳወቅ) እሞክራለሁ›› በማለት ለኤፍ.ኤም. ጋዜጠኛ ነኝ ባዩ ደዋይ የንግግሩን ቀጣይነት የሚያበስር ምላሽን ሠጠው፡፡
በነገሩ የተደሰተ በሚመስል ጥርት ያለ ድምፅ ‹‹በጣም
ጥሩ በመጀመርያ ሙሉ ስሞትን እና ከየት የሀገራችን ክልል እና ከተማ እንደሆኑ ይንገሩን›› በማለት የመጀመርያውን ግን የማያስሸልመውን
ጥያቄ በማስቀደም ወደሚያስሸልሙት ጥያቄዎች ተሸጋገረ፡፡
ጋዜጠኛው ቀጥሏል
‹‹የመጀመርያው ጥያቄ ይሰማል
አድማጫችን (እከሌ) አጠገብህ ሬድዮን ካለ ሙሉ ለሙሉ ዝጋው››፡፡
የወዳጄ ወዳጅ በቶሎ ቀበል አድርጎ ‹‹ኣረ ምንም ሬድዮን አጠገቤ
የለም ዝግ ነው›› በማለት መለሰለት፡፡
‹‹ መልካም፣ የመጀመርያው ጥያቄ፣ የህዳሴው ድልድይ
የሚገኝበትን ትክክለኛውን የሀገራችንን ክልል ጥቀስ………መለሠለት ……….. ትክክለኛውን መልስ መልሠዋል…….. ቀጣዩ ጥያቄ……››፡፡
እያለ እያለ ጋዜጠኛው ሶስቱንም ጥያቄ ሲጠይቅ፣ ተጠያቂውም መልሱን አንድ በአንድ በትክክል በመመለስ የ 5000 ብር ተሸላሚነቱን
አረጋገጠ፡፡
መቋጫው ላይ፣ ‹‹የአብሮነት ቆይታችን ከማብቃቱ በፊት፣
ቀደም ሲል በመግቢያችን ላይ የጠቀስንልህን የገንዘብ መጠን አሸናፊ በመሆንህ፣ ሽልማቱን ትራንስፈር ይደረግልህ ዘንድ በአቅራቢያክ የሚገኝን የባንክ ስም አልያም የባንክ አካውንትህን ትነግረናለህ››
፡፡
ማመን እያቃተው፣ የባንክ የአካውቱ ረዘም ያለ ስለሆነ
በቃሉ ስለማያስታውስ ብቻ ፈጠን ብሎ በሚኖርበት ከተማ የሚገኝን አንድ የባንክ ስም በመጥቀስ ሠጠው፡፡ ከስልኩ በስተጀርባ ያለው
ጋዜጠኛ የሰማውን ባንክ ስም እና ሙሉ ስሙን ደግሞ ሲጠራ ‹‹ አዎን ›› የሚለውን የማረጋገጫ መልስም ከወዲህ ቢያገኝም የቀረ ሀሳብ እንዳለው ያስታውቃል፡፡
የወዳጄ ወዳጅ በዚያው ቅፅበት በውስጡ ‹‹… ደግሞ ምን
ቀረ…..›› እያለ ቀጣዩን ሀሳብ ማዳመጥ ጀመረ፡፡
‹‹….. እንግዲህ አድማጫችን የዝግጅታችን ተካፋይ ሆነው
ለተጠየቁት ጥያቄ ሙሉ መልስ በመመለሶ ተሸላሚ ስለሆኑ በሬድዮን ጣቢያችን
እና በእስፖንሰራችን ስም በድጋሜ እንኳን ደስ ያሎ ለማለት እንወዳለን፡፡››
‹‹…ለህዳሴውን ድልድይ ግንባታ ቀጣይነት ያለው ርብርብን
በማስቀጠል ረገድ እርሶም እንደ አንድ ዜጋ ያለቦትን የዜግነት ድርሻዎን ይወጡ ዘንድ በኤሌከትሮኒክ ስልክ በአዲስ መልኩ እየተሸጠ
ያለውን የ500 (አምስት መቶ ብር) የቦንድ ግዢ 5 (አምስት) ባለ መቶ ብር ካርዶችን ፍቀው በመላክ ለዚህ ታሪካዊ የተቀደሰ አላማ
አካል ይሁኑ ዘንድ መልካም ፍቃዶን እንጠይቃለን፡፡›.… ለነበረን
መልካም ቆይታ እናመሰግናለን ደህና ይሰንብቱ፡፡›› ይለውና በመሰናበት ስልኩ ከወድያ ይዘጋል፡፡
ስልኩን ከዘጋው ቡሀላ ሀሳቡ በሁለት
ቦታ ተከፈለ እደለኛነት አልያ እድለቢስነት፡፡ በንጋታው ወደ ጋራ ወዳጃችን ስልኩን ያጮሀል (ምክንያቱም ይህ የጋራ ወዳጃችን የቴሌ
ሠራተኛ ነውና)
‹‹...እውን እንዲህ አይነት ነገር አለ...... 500 ብሩን ልክፈል አልክፈል›› በማለት ይጠይቀዋል፡፡
በተጨማሪም ጉዳዩን በሠፊው ካብራራለት ቡሀላ ቁጥሩን ሠጥቶት ይሰናበታል፡፡
የቴሌው ወዳጃችን ጉዳዩ ስላስገረመው ኮምፒውተሩን ከፍቶ የቁጥሩን ባለቤት ተመለከተው፣ በግለሰብ ስም ነው የተመዘገበው፡፡ የደወለባቸውን
የስልክ ቁጥሮች ዝርዝር ያወጣለት ዘንድ የሚጠይቀውን ሳጥን ሲጫን 0920 የሚሉ ቁጥሮችን ብቻ ነው የሚደውለው፡፡ ቅድም ሲመለከት
የነበረበት 74 ብር 369 ብር ሆኖ ሲያየው ጭራሽ የማወቅ ፍላጎቱ ጨመረ፡፡ አሁንም ሳያመነታ ከደወለላቸው ሰዎች ዝርዝር አራቱን
በመምረጥ ደወለላቸው፡፡
‹‹ከቴሌ ነው እንዲህ እነዲያ………. የሚል ሠው ደውሎ ነበር›››
ከወድያ ‹‹ አዎን በእናትህ እስከዛሬ እየተበደርኩ በተለያየ
ግዜ አንዴ ዳታቤዝ አንዴ አካውንትህ ጠፋብን ምናምን እያለኝ 400
(አራት መቶ ብር) ከላኩለት ቡሀላ ………››፡፡
የሚቀጥለውም ጋር ደወለ ሴት ነበር ያነሳችው ‹‹500 ብር ልኬለታለሁ ግን እስካሀን
ምንመ ብር አላከልኝም››፡፡
ሶስተኛው ጋር ደወለ ‹‹ አዎ ደውሎ ነበር ግን ሰምቼ ብቻ ነው ዝም ያልኩት›› ፡፡
የመጨረሻው ጋር
ደወለ ‹‹……. 500 ብር ተበላሁኝ ማለት ነው…›› በሚል የቁጭት ጥያቄ አዘል መሳይ መልሱን ሠጠው፡፡
ነገሩ ይበልጥ ሲያስገርመው እና ድፍረቱ ሲያስደንቀው፣
ቀጥታ ወደተባለው አስገራሚ የኤፍ.ኤም ጣቢያ ስልክ ቁጥርን ከኮምፒውተሩ እያመሳከር እፍለፊቱ ካለው የቢሮው ስልክ ላይ……
ጠቅ ……. ጠቅ …….ጠቅ አድርጎ መነጋገርያውን ወደ ጆሮ አስጠጋ
ከወድያ ይጠራል ……. ጡጥ ……. ጡጥ …….
አኒቲ ነኝ
አኒቲ ነኝ
ይቀጥላል!

Comments
Post a Comment