በዚህ በኩል - ህጉን ጣስሽ ብሎ፣ ያመናጭቃታል
የደኑ ጥበቃ፣ ይተናኮላታል፣ ሊያስር ያሳዳታል
ሸክሟን ያስጥላታል፣ በባዶ ይሰዳታል
ለእሷ ምግቧ ነው፣ ጉርሷ ይጨንቃታል፤
እውነት ለመናገር፣ አሷስ መቼ ጨንቋት
ከእሷም ጉርስ በላይ፣ አለ ሚያሳስባት
እንዲ አስጠግርሮ፣ ወገቧን ሚቆርጣት
የሀረጓ ቅጣያ፣ የማህፀኗ ክፋይ፣ የይሆናል እዠት
መቼስ ገመተና? ይችል እንደሆነ፣ አንድ እንኳ
ሊኖራት፤
ሲርበው የሚያለቅስ፣ ሲጠግብ የሚቧረቅ፣ ሄኔ
ያስተኛችው
ማንያውቃል ይኖራት ይሆናል፣ ባለማወቅ ብቻ፣ ብዙ
የወለደቸው
ተርቦ ሚገባ፣ ይማርልኝ ብላ፣ ትምህርት የላከቸው፡፡
ተሸክማ ደክማ፣ ጎብጣና ገርጥታ፣ ሆና ያልተሻለች
ከዛሬ ህይወቷ፣ የተሸለ እንዲኖር፣ ለልጇ የተመኘች ፤
አመጣጡን ያውቃል፣ ጠንክሮ ይማራል
ከግቡ ላይ ደርሶ፣ ላቤን ይጠርገዋል ፤
ምን ያደርጋል ታድያ፣ በሕልም ዓለም ስትስል
ተጨናገፎ ቢቀር፣ የልቧን ሣያክል::
ዛሬን እንዳረጀች፣ የጇን መች አገኘች
ህልሟ መች ተሳካ፣ መች ምኞቷን ኖረች
ከአሁን ቡሀላ፣ መችስ ትኖራለች፤
ተስፋዬ ያለችው
ገና ነፍሱን ሳያውቅ፣ ሱስ ቀድሞ እያወቀ
ጠንክሮ እንደመስራት፣ በወሬ እየሞቀ፤
ላይብረሪ እያለ፣ ፑል-ቤት ሄዶ መዋል
አዳር ላጥና ብሎ፣ በጭፈራው መጋል
ከማይሆኑ ገጥሞ፣ እነሱን ለመምሠል፤
ልፋቷን በትኖት፣ ዋልጌ ሆኖ ቀረ፣ ገና በ ሀይ-እስኩል፡፡
ከወገቧ ጉብጠት፣ ከሸክሟም ክብደት
ልቧ እንዳይሠበር፣ ሁሉም ፍቅር ይስጣት
የኛ እናት ባትሆንም፣ በሠፈር ካወቅን፣ እንደዚህ
ያለች ሴት
ብቻዋን እንዳቱል፣ ሄደን እናጫውታት፣ ካለንም
እንርዳት
በዓልም ሲደርስ፣ እንሂድ እናፅናናት፣ እንደ
ልጅ እንሁናት
ቸርቻሪ፣ ለቃሚ፣ ቃራሚ፣ ብትሆንም ወጣት፣ ያደፈች
አጎሪት
እኔ እንደ ሚመስለኝ፣ እናት ያው እናት ናት!
መታሠቢያነቱ
ልጆቿን ሠው ለማድረግ ተቸግራ፣ አርዛ፣
ተንቃ፣ ተጎሳቁላ፣ ርቧት እና ጠምቷት የእጇን ሳታገኝ
እስካሁን ሕልሟን ላልኖረች፣ እንዲሁም ምኞቷን
ለሞተች እናት ይሁንልኝ፡፡
aniti
© ሰኔ 25፣ 2005 ሐ
Comments
Post a Comment