Skip to main content

እማማ በላይነሽ

ዛሬ ምነው አኒቲ ወሬ አበዛ እንዳትሉኝ፡፡ መቀባጠር ነው ብላችሁ ከሆነም በዓመት አንዴ እንድቀባጥር ከፈቀዳችሁልኝ እሰየሁ ዝቅ ዝቅ ሳቅ ሳቅ እያላችሁ አብራችሁኝ ዝለቁ፡፡
መቼም በዝህች ዓለም ላይ ስንኖር፤ በዕለት ተዕለት ንሮአችን፣ ማለትም በቤታችን፤ በሰፈራችን፤ በትምህርት ቤት፤ በስራ ቦታ፤ ሌላም ሌላም ቦታዎች የሚያጋጥሙን ከንፈር አስለጣጭ፤ ጥርስ አስከፋች ገጠመኞች ሊኖሩን ግድ ይላል፡፡

እናላችሁ ቀጥዬ የማወጋችሁን ገ

ጠመኝ ያካፈለችኝ አንድ የሥራ ባልደረባዬ ስትሆን ግዜው ቢቆይም (ያኔ በየሰፈሩ እና በየ ስራ ስሩ ስለ ኤች.አይቪ ማስተማር ብርቅ በነበረ ወቅት) እኔ የሰማሁት በዚሁ ዓመት በመሆኑ ለራሴ ብቻ ለምን ልገረም ብዬ (ያው መቼም ከናንተ የምደብቀው ነገር የለኝምና) ላካፍላችሁ ወደደኩ፡፡

ቦታው ኦሮሚያ ክልል አንቦ ከተማ አከባቢ ይመስለኛል ባልዘነጋው፡፡ የምላችሁ ወዳጄ ስለ ኤች.አይ.ቪ. ኤድስ እና ስለ ኮንደም ለከተማው ሴት ማህበራት እንድታስተምር ትጋበዝና ወደ ስፍራው ታቀናለች፡፡

ትምህርቱ ተጀመረ
ተሳታፊወቹ ሴቶች ሲሆኑ ያው መሪ መኖሩ አይቀርምና በመሀላቸው የተለያዩ ተሰሚነት ያላቸው የየእድር መሪዎች ይገኙበታል፡፡ ከነኚህም ሴት መሪዎች መካከል ይህን ፅሁፍ ለመፃፍ ያበቁን እማማ በላይነሽ ይገኙበታል፡፡ እማማ በላይነሽ በከተማው የእድር መሪ ብቻም ሳይሆኑ ተሰሚነት ካላቸው በጣት ከሚቆጠሩ ቆፍጣና እና ቀብራራ ወዛዝርት መሀል አንዷናቸው፡፡

ወዳጄ ማስተማሩን ቀጥላለች (በነገራችን ላይ እድሜዋ ገፋ ያለ ሲሆን ምንም እኩል ባይሆንም ወደ እማማ በላይነሽ እድሜ ሰፈር ከአስር እና አስራ አምስት አመታት ቀደም የሚል ነው)፡፡ 
መቼም ስለ ኤች.አይ.ቪ. ኤድስ እና ስለ ኮንደም ለማስተማር ከምንጠቀማቸው ነገሮች ውስጥ ሁለት ዋና ዋና የማስተማሪያ ቁሶችን ጥቀሱ ቢባል በናንተ ስለምተማመን በጥሩ ሁናቴ የተመሰለ የወንድ ብልት እና እራሱ ኮንደምን እንደምትጠቅሱ ጥርጥር የለኝም፡፡

ከዛስ አትሉም፤ ከዛማ ትምህርቱን እያስተማረች ያለችውን ወዳጄን የአንድ ሠው አኳዃን እየጨነቃት እየጨነቃት መጣ፡፡ የማን እንደማትሉኝ አውቃለሁ አማማ በላይነሽ እንደምትሆን ስለምትገምቱ፡፡ 

አስተማሪዋ ወዳጄ ኮንደም፤ የወንድ ብልት፤ የሴት ብልት፤ ውሽማ ምናምን ምናምን ባለች ቁጥር እሳቸው እሳት እንደነካው ፔስታል አንዴ ወደ ግራ አንዴ ወደ ቀኝ ፊታቸውን በሽሙጥ ያጣሙት፣ ያጨማድዱት እና ያኮማትሩት ነበር፡፡ አንዳንዴ ደግሞ ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ ሌሎች የትሬኒንጉ ተሳታፊ ወዛዝርት እንዲሰሙ አድርገው

"ኡኡቴ አልቀረብሽ እቴ" 
እያሉ እንደ ታዋቂው እና የኳስ አዋቂው የማንሲቲና ጣሊያናዊ አጥቂ ባላቶሊ የተሰማቸውን እያደረጉ ትምህርቱን ልክ እንደ ደውል ሳያቋርጡ በየ 15 እና 20 ደቂቃ እያሸማቀቁ አስቸግረዋል፡፡ ታድያ ወዳጄ ማንነታቸውን የማታውቅ ሲሆን የሚያደርጉትም ነገሩ ስላላስቻላት የፕሮግራሙን አስተባባሪ በመጥራት

"በንጋታው እሳቸው እንዳይመጡ አድርግ ሌላው ሠው እንዳይቀበል እና እንዳይማር እያደረጉ ነው"
ስትል እንደ መናደድም እንደ ማማርም እያለች ነገረችው፡፡ አዘጋጁ ከት ብሎ በመሳቅ ወድያው መልሶ ፊቱን እያኮሳተረ ትኩረቱን የወዳጄ አይን ላይ በመትከል 

"ኣረ በጭራሽ አይሆንም እሳቸውን አባረርን ማለት ስራችን ልክ ድንጋይን በኳስ ለመፍለጥ የመደብደብ ያፍል አደረግነው ማለት ነው" 

በማለት ያላቸውን ተሰሚነት ያጫውታት ጀመረ፡፡ 

"እማማ ብርቄ ማለት ለዚህ ከተማ እድር እና ወዛዝርት ልክ እንደ አንድ ብርጌድ መሪ ጄነራል ናቸው፡፡ ወዛዝርቶቹ ደግሞ ለእሳቸው እንደ እግረኛ ጦር አባላት ናቸው፡፡ በዚህ ሂዱ በዚያ ምጡ ካሏቸው መሄድ ብሎም መምጣት ብቻ ነው፡፡ እናም ሙሉ ትሬኒንጉን ጥለው እንዲሄዱ የማድረግ እድላቸው የሰፋ ነው"

ካለ ቡሀላ፣ ንግግሩን በጥያቄ አጠቃለለው፡፡ 

"ይልቅስ ሌላ ዘዴ ካለሽ መሞከር ይሻላል እንጂ ይሄ አያዋጣንም" ይላታል፡፡
ነገሩን በፍጥነት የተረዳችውን ወዳጄ ሌላ መላ ከመምታቷ ቀድመው እማማ በላይነሽ በንጋታው ጥዋት እንደገቡ የቀኑ ትምህርት ገና ከመጀመሩ፣ 
"እጁን ያወጣ ይሸለማል!" 

የተባለ ይመስል ለመጠየቅ ኪሚወጣው ከፍታ በላይ የባንድራ መስቀያ የሚያክለውን እጃቸውን ወደ ሰማይ ቀሰሩት፡፡ ወዳጄ በመደነቅ ብሎም፣ የሰሙት ነገር አለ እንዴ? ብላ በመደናገጥ፣

"አቤት እማማ በላይነሽ ምን ነበር?" 
ብላ ላወጡት ረጅም እጅ መመለሻ መፍትሄ ሰጠቻቸው፡፡
እማማ በላይነሽም የወዳጄን የመልሶ ማጥቂያ ጥያቄን ማስጨረስ ሳያስፈልጋቸው የማሸማቀቂያ ጥያቄያቸውን ሰነዘሩ፡፡

"እኔ የምልሽ፤ እንደው ምን ሥራ ብታጪ ነው ይሄን በዚህ እድሜሽ የምትዘላብጂው? ኣረ እቴ! ምነው ሸዋ! ጉሊት እየሸጥሽ ብታድሪ ይሻልሻል፡፡ እቺህናት በላይነሽ!"

አሉና ጥያቄያቸውን አማራጭ መፍትሄ የሚመስል ወግ አሳዝለው በግርምት እና በትንግርት የተዘረጋውን ነጠላቸውን በማስተካከል አክትመውት መልስ በሚጠብቅ ስሜት ዝም አሉ፡፡ 
አሰልጣኟ ወዳጄ በተዘበራረቀ ሀሳብ ውስጥ ለአፍታ እንደማሰብ ካለች ብዃላ፡፡ ነገሩን ለማቃለል ስትል ቀልድ አስመስላ ሳትወድ በግድ፣ ልክ የሚያስተምረውን ትምህርት በደንብ አጥንቶ ሳይመጣ የማያውቀውን ጥያቄ በተማሪዎቹ እንደተጠየቀ መምህር እየሳቀች፤ ጉዳዩን በሌላ የትሬኒንጉ መልመጃ አረሳሳቻቸው፡፡

ወዳጄ የምትሰጠው ትሬኒንግ ሊያበቃ አንድ የመጨረሻ ቀን እንደመቅረቱ፡፡ የሰጠችውን አስተምሮት ተቀባይነት የውሀ ሽታ እንዳይሆን ብላ በመስጋት፣ በዛሬው የምሳ ሠዓት እማማ በላይነሽን በምሳ ግብዣው ላይ ለማስረዳት ቆርጣ ተነሳች፡፡ አይደርስ የለ ምሳ ደረሰ ከእማማ ጋርም ተገናኘች፤ አወራች፤ አስረዳች፡፡

በጥቂቱም ቢሆን ተረዱላት ቀረቧት ብሎም የነበረባቸው ቅርፊት በወዳጄ ትህትና፣ ስለተሸነፈችላቸው ነው ሚመስለኝ ግን ተቀረፈላቸው፡፡ በዚህም የተነሳ የዛሬው ከሰዓት ትምህርት ከወትሮ በተለየ ሁኔታ ሰኪክ ሆኖ አሰልጣኟ ወዳጄን ለመጀመርያ ግዜ ሳያሸማቅቅ ተጠናቀቀ፡፡ ወዳጄም በእለቱ የመዝግያ ንግግሯን እንዲህ በማለት በማድረግ ቀኑን ቋጨቸው፤
"እንግዲህ እናቶቼ፣ እህቶቼ የእስከዛሬው የመማማር ቆይታችን በነገው እለት የሚያበቃ ሲሆን፣ እኔ እስከዛሬ አስተማሪ ነበርኩኝ ነገ ግን ከእናንተ ከሰልጣኞች ውስጥ 3 ሠዎችን በመምረጥ የእስከዛሬውን ትምህርት በተግባር በመታገዝ የምታስተምሩ ሲሆን፡፡

የመጀመርያዋ ተመራጭ ወይዘሮ፣ ለተሰብሳቢው የኮንዶምን ጥቅም በተማረችው መሰረት ታስተምራለች፡፡ ሁለተኛዋ ደግሞ፣ አገልግሎቱ ያልተበላሸን ኮንዶም እንዴት እንደምንለይ በተማርነው መሰረት ታሳየናለች፡፡ የመጨረሻዋ የነገዋ ተመራጭ አስተማሪ ደግሞ፣ ኮንዶምን እንዴት በወንድ ብልት ላይ እንደምናጠልቅ በናሙና የወንድ ብልት በመታገዝ በትምህረታችን ወቅት ባየነው ስእላዊ ትምህርት መሰረት በተግባር ታሳየናለች፡፡ ስለዚህ ሁላችሁም ተዘጋጅታቹበት እንድትመጡ የሚመረጡት ሰዎች ነገ ስለሚታወቅ፣ ያልገባቹ ነገር ካለ በግል ዛሬውኑ ልትጠይቁኝ ትችላላቹ ለዛሬ ጨርሰናል"፡፡

ዛሬ ቅዳሜ ነው፡፡ ብሎም የስልጠናው የመጨረሻ ቀን እና ሠንበት እንደመሆኑ መጠን፣ አበል ይከፈላል፤ የትምህርቱ የተግባር መልመጃ (Demonstration) በተመረጡ ሰልጣኝ ወዛዝርቶች ይከወናል፡፡ 

መቼም እንደምታውቁት የእኛ ሰው ህዝብ በተሰበሰቡበት እና በሚበዙበት አካባቢ፤ ለምሳሌ በሠርግ፣ በለቀሶ ቤቶች፣ እቁብ ላይ ገንዘብ ለመውሰድ ሲል፤ ወዘተም ላይ ሳይቀር lol፣ እንዴት ሽክ ብሎ እንደሚለብስ ታውቁት የለ፡፡ እስኪ አስቡት ለዛውም ለእድር ሀላፊ ወዛዝርት ማን ይነግራቸዋል እንዴት ሽክ እንደሚሉ? ኣረ ማንስ ያክላቸዋል? ኣረ ማንም አትሉም? 

እናላቹህ፣ ለዚህ መጨረሻ ቀን ሁሉም ወዛዝርት የክት ቀን ጥበባቸውን ተጠበውት፣ ነጫጭ ነጠላውን በላዩ ላይ አደደግድገዉት በጥዋት በመምጣት፣ ከመድረክ ለሚመለከት ሠው አዳራሹን የነጭ ሻማ መጋዘን አስመስለውታል፡፡ 

ወዳጄም በፋንታዋ ለተግባር መልመጃው ስትል ያመጣችውን ኮንዶሞች፣ በራሪ ወረቀቶች፣ እንዲሁም የተዘጋጁ የተግባር (Demonstration) ማሳያ የወንድ ብልት ናሙና(Sample) ጭምር በአደራሹ መድረክ ላይ በሚገኘው የአሰልጣኞች ጠረፔዛ ላይ አኖረቻቸው፡፡ 

በነገራችን ላይ የተለያየ አይነት የወንድ ብልት ናሙና(Sample) ያለ ሲሆን፣ እነሱም ከእንጨት እና ከጎማ (Rubber) የሚሰሩት ዋናዎቹ ሲሆን፡፡ እንደምታውቁት ሁለቱንም አንድ ከሚያደርጋቸው ነገር አንዱ እንደ አክሱም ሀውልት ቀጥ ብለው መቆማቸው እና ትክክለኛ የወንድ ብልት ቅርፅ እና መልክ መያዛቸው ሲሆን፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሳላወራውም እንደምታርፉት፣ ከጎማ (Rubber) የሚሰራው የወንድ ብልት ናሙና (Sample) ከእንጨቱ በተሻለ መልኩ ትክክለኛ ከሚያስመስሉት ነገሮች ውስጥ፣ አንዱ የሚሰራው በፋብሪካ እንደመሆኑ መጠን የሚቀባው ቅብ ከእንጨቱ በተሻለ ሁኔታ ቁጭ ቁርጥ ነው፡፡ በሌላ መለያ ደግሞ ከጎማ (Rubber) የሚሰራው የወንድ ብልት ናሙና(Sample) በእጃችን በምንነካው ወቅት፣ ልስላሴውና እንደ እንጨቱ ያለመድረቁ አውነትም ጋሽ ብልት አለም በቃኝ እኔን ያየ ይማር ብሎ በፈጣጣው እራሴን ችያለው ብሎ በግሉ ከወንዶች ህይወትን ተካፍሎ የመጣ አስተማሪ ያስመስልበታል፡፡ 

ያልኳቹ አስልጣኝ ወዳጄም ይዛው የነበርው ናሙና ይሄ የጎማውን መሆኑን ያዙልኝ፡፡
የምታውቁትን ነገር ቀባጠርኩ አይደል? ይቅር በሉኝ ወደ ዋናው፣ ወደ ገደለው ጉዳይ ተመልሻለው፡፡ 

እናላችሁ አሰልጣኟ ወዳጄ ይህንን ናሙና ከሻንጣዋ አውጥታ ለመጀመርያ እና ለመጨረሻ ግዜ በዚህ አዳራሽ ተሰብሳቢ ፊት ስታስቀምጠው፣ አዳራሹ በጉርምርምታ ተሞላ፡፡ ከታዳሚዎቹ ወዛዝረቶች አብዛኛው የነጠላውን ጫፍ በአፉቸው ላይ እያኖሩ እና በግላጭ ለማየት የጓጉ ይመስል ቁጭ ብድግ እና ልክ የቴብል ቴኒስ ውድድር እንደሚመለከት ወጣሪ ደጋፊ አንገታቸውን ከግራ ቀኝ የሚወዘውዙ በዝተዋል፡፡ 

መቼስ የስልጠና መጀመሪያ እና መጨረሻ ቀናት ላይ ባለስልጣናት ያለመጥፋታቸው ነገር ጥሩ ጎን ሆኖ፣ ከፊት ወንበር ላይ ተጋባዥ ሆና የተጠራችው የከተማው የሴቶች ጉዳይ ሃላፊ በመኮሳተር እና ድምጿን ከፍ በማድርግ

"አንድ ግዜ ፀጥታ ይከበር!" 
ስትል ማንባረቋ ተሰብሳቢውን ረጭ አደረገው፡፡ ብሎም በዚህ አጋጣሚም የመጨረሻው ቀን ትሬኒንግ በግዜ ለማብቃት እንደሆነ በመጨመር ጀመረች፡፡ አሰልጣኟ ወዳጄም በንግግር፣ መድረኩን እንድትመራ እና የመጨረሻ የስልጠናውን ክፍል እንድታመቻች ዘንድ፣ የመረጠቻቸውን ሶስት የተሳታፊ አስተማሪ ወዛዝርቶችን ስም ዝርዝር ለተጋባዧ የሴቶች ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ በመስጠት ፊት ለፊት በሚገኘው የተማሪዎች ወንበር ላይ ሄዳ ተቀመጠች፡፡
ተጋባዧ ባለስልጣን አፈቀላጤ የስልጠናውን ጠቀሜታ መልሳ በማስታወስ ስልጠናውን ለማስጨረስ አስጀመረች፡፡ 

በመቀጠልም የትምህርቱ ማብቂያ ወደሆነው ክፍለ ግዜን ማመቻቸቱን ጀመረች፡፡ 

"እንግዲህ ትላንት አሰልጣኛቹህ እንዳሳወቀቻችሁ እስከዛሬዋ ቀን ድረስ፣ በእዚህ አዳራሽ ውስጥ ባሳለፋችሁት የስልጠና እና የተምህርት ጊዜን ውጤታማነት ለማሳየትም፡፡ እንዲሁም እናንተ የተረዳቹበትን ደረጃ ለመገመት ያመቸን ዘንድ 3 ሴቶችን የመረጥን ሲሆን አንድ በአንድ እየጠራዃቹ ትላንት ለሁላችሁም የተሰጣችሁን ርዕስ የምታብራሩልን እና የእስከዛሬውን ትምህርት የምትከልሱበት ግዜ ይሆናል፡፡" 

በማለት አሰልጣኟ ቆፍጠን ቀጠን ባለ አማረኛ ከተነተነች ቡዃላ፣ ወዳጄ የሰጠቻትን ወረቀት ሁለት እጇን በማስተባበር መዘረጋጋቱን ጀመረች፡፡

አመቻቿ ወደ ድምፅ ማጉያው ማይክራፎን በደንብ በመጠጋት 

"አንደኛ ወ/ሮ ሮማን በሻ፣ የኮንዶምን ጥቅም በተማሩት መልኩ እዚህ መድረክ ላይ………………"

ብላ ሳትጨር 
ቸብ….ረብ……ቸብ…..ረብ በሚል ድምፅ፣ አዳራሹ የእርምጃን እስቴፕ በሚጠብቅ መልኩ በጭብጨባ ቀለጠ፡፡

ወ/ሮ ሮማን ተነሱ ወደ መድረክ በቀለጠ ጭብጨባ ታጅበው፡፡ ………. አንድም ሳያስቀሩ ትምህርቱን ጨረሱ፡፡ ሲመለሱ ተሰብሳቢው አሁንም በጭብጨባ፣

ቸብ….ረብ……ቸብ…..ረብ እያደረጉ እንደ ደርግ ባለስልጣን ጀነን ብለው ከተነሱበት ወንበር ደርሰው ሲቀመጡ ጭብጨባውም አበቃ፡፡

"ሁለተኛ………" 
አለች እና ተጋባዧ እንግዳ ማመቻቸቷን ቀጠለች፡፡ 
በቃ ሁለተኛዋም ወ/ሮ ጀመረች ጨረሰች፡፡ እሷስ ለምን ይቅርባት ተብሎ የሚጨበጨብ በሚመስል ቸቸብ….ረረብ……ቸቸብ…..ረብ ሪትሙን ባይጠብቃትም አልተለያትም ነበር፡፡

በነገራችን ላይ የመጨረሻው የቤት ስራ እኔ አራሱ ሳስበው የሚከብድ ይመስለኛል፣ አይመስላቸሁም?፡፡
ለዛውም ወዛዝርቶች ተነስተው ወዛዝርት ፊት ለፊት ነብስ ያለው መሳይ ብልት ይዘው ማስተማር ማሳየት፡፡

ጉድ እኮ ነው አለች እቴቴ! እንደው ይሄ አይነቱ ገጠመኝስ በእናታችን ወይ በአያታችን አያድርስ ነው እንጂ. . . . . . 

አይደርስ የለ የሦስተኛው ተማሪ ተራ ከች ብሎ ደረሰ፡፡

"ሦስተኛዋ …….." 

ብላ መጣራቷን ስትጀምር፣ አዳራሹ ልክ እንደ እኔ የቤት ስራው እንደሚከብድ ነቄ ብለዋል መሰለኝ መቁነጥነጥ ጀመሩ፡፡

መቼም መጠራቱ አይቀር ጥሪው ቀጠለ፡፡

አመቻቿ "ሦስተኛ ወ/ሮ በላይነሽ (በቦተሊካው አጠራር ሆነ እንጂ እማማ በላይነሽ ማለቷ ነው)፣ የመጨረሻውን የቤት. . . . . . "

ብላ ሳትጨርስ አዳራሹ በወዛዝርቶች ማጉረምረም እና በአንዳንዶች የአቃጣሪ እና የሽሙት ጎሽዮሽ ሳቅ ድብልቅልቁ ጠፋ፡፡
ሳይቆይ ግን የባለስላጣኗ መኮሳተር እና 

"አንዴ ፀጥታ!" 

የሚለው ማስፈራሪያ አዘል መልእክት ሲከተል ሁሉም ድምፁን አጣፋ፡፡ በምትኩ ግን በሚገርም ሁኔታ እጃቸው እስኪቃጠል ድረስ ማጨብጨቡን ተያያዙት፡፡ እውነቴን ነው እንዲህ ያለውን ጭብጨባ ውጪ ሆኖ ለሚሰማ ሰው ጭብጨባው የደርግ ግዜ ባለስልጣን ሳይሆን እራሱ መንግስቱ ሀ/ማርያም ለንግግር ወደ መድረክ እየወጣ ያለ ነው ያስመሰሉት ስላችሁ፡፡ 

እናም እማማ በላይነሽ የጭብጨባው ድምፅ የነዘራቸው ይመስል ከተቀመጡበት ተወንጭፈው እየተነሱ 

"ጉድ በል ጎጃም! ኡኡቴ አልቀረብሽም እያንዳንድሽ!" 

አያሉ በግርምት ተሞልተውም ቢሆን ወደ መድረኩ ማዝገም ጀመሩ፡፡ እንዴት እንቢ ሳይሉ ካላችሁኝ፣ አንደኛ ትላንት ተግባብተዋል ሁለተኛ ደግሞ ባለስልጣን፣ ለዛውም የሴቶች ጉዳይ፣ አለች፡፡ ሶስተኛው እና ዋናው የአበሉ ጉዳይ ነው ባይነኝ፡፡
የሆነው ሆኖ፣ ቀደም ሲል እንደነገርኳችሁ እማማ በላይነሽ በእድር አመራራቸው እና ደፋር ውሳኔ ሰጪነታቸው ብሎም በመድረክ አያያዛቸው አንቱታን ያተረፉ ብቃት ያላቸው ደሞዝ እና ፖለቲካ አልባ መሪ ናቸው፡፡ በቃ ደረሱ መድረኩ ላይም ወጡ፡፡ አቤት ግርማ ሞገስ አቤት ቁመና በነጫጭ ልብሶቻቸው አምረው ለሚመለከቷቸው ወሬኛ ሁላ፡፡ 
ተጀመረ 

መድረኩ ላይ ቆመው እንዳለ፣ ድምፃቸውን ከፍ እያደረጉ፣

"ወይ ጉድ እቴ!"

እያሉ ነጠላቸውን በቀኙ እና በግራውም ትከሻቸው ትክክል ቁልቁል ጥለቱን እንደ ቀለበት መንገድ በትይዩ ቀጥ አድርገው እያደገደጉ አሳመረው አስተካከሉት፡፡ አስተካክለው ሳይጠግቡ ይመስል በባለስልጣኗ አመቻች አማካይነት የተሰጣቸውን የወንድ ብልት ናሙና (Sample) እንደው ፈራ እና ኮራ እያሉ እንደ ሽልማት በሁለት እጃቸው ተቀበሉት፡፡ 
እስከዚች ሠዓተወ ድረስ የሚጨበጨበው ጭብጨባ ቀጥ አለ፡፡ በፋንታው ግን የጉጉት ያህል በአደራሹ ወደ ቀኝ እና ወደ ግራ የሚወዛወዙ የተሳታፊ ወዛዝርት አንገቶች አሁን ከቅድሙ በበለጠ ሁኔታ የማሸነፍያ የቴኒስ ሰርብ ይመስል በጣም በዝተዋል፡፡

ምን ያድርጉ አንድም ትእይንት ብሎም ትምህርት እንዳይቀርባቸው ይመስላል፡፡ አልቀረባቸውም ድንቄም ትምህርት እሱንስ ተዉት ሆድ ይፍጀው ……. 

እማማ በላይነሽ ግን፣ 

ግር ያላቸው ነገር ያለ ይመስል ለመጀመርያ ግዜ የነኩትን ይህን ጉኡዝ ነገር ትኩር ብለው በማየት ያገለባብጡት ጀመረ፡፡ ሳያስጠጡም ጨ……መ…….ቅ ጨ……መ…….ቅ አደረጉት፡፡ 

ከዛም አንገታቸውን ወደ ተዘጋጀው የድምፅ ማጉያ የአግርሞት ቱክረታቸውን ሳይነቅሉ ጠጋ እያደረጉ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ግርምት በተሞላ ድምፅ

"ሆሆ ኡኡቴ. . . . . . . 
ወይ መድሃንያለም. . . . . . . . . .

እንደው ባኖርከኝ አርባ አታት አንዴም በግላጭ የማላውቀውን ዛሬ በአደባባይ በስተእርጅና ታሳየኛለህ. . . . . . . .

አሄ. . . . . . ሄ "

አዳራሹ የንብ መንጋ የመጣ በሚመስል ድምፅ ለረጅም ሰዓት በሳቅ ተሞላ፡፡ ፍርፍር ብለው ከሳቁት ውስጥ አንጀቷን ያደረሰችው አሰልጣኟ ወዳጄ አንዷ ናት፡፡
እማማ በላይነሽም የሚጠበቅባቸውን ሁላ አስተምረው የተሠጣቸውን እድል በመጠቀም ልክ እንደ አድራቸው፣ መድረኩን እስክበው ወረዱ፡፡ 

አበቃሁ


አኒቲ ነኝ

መጥፎውን በመልካም
ጎኑ እንጠቀምበት፡፡

Comments

Popular posts from this blog

The Historic Chaltu Speeks Out

Let me paint you the picture of what happened in ATL yesterday. Me and Riyad S abona walking, minding our own business and we see an anti-Jawar protest happening 200 yards away from the meeting entrance. The police directed us to walk in closer to the side of the protest to avoid obstructing traffic.  So we saw their flags and I decided to take out my Oromo flag and walk.  First, it was just the slurs, calling me Galla. Then it was the spit, in front and behind me and then one made it with the perfect aim to hit my cheek. I continued to walk with my head high with the utmost respect until one 'balance' thought it would be okay to reach over and snatch my flag. He thought he got the flag, but I killed that dream, but as soon as he reached again and grabbed my hijab, I turned around and his face hit the back of my hand (like how words can change everything?). Lol, I actually slapped the hell out of him. When I looked back they were grabbing on Riyad's trad...

ከዶ/ር መረራ አስለቃሽ ጭስ አንዷ

ዶር መረራ ጉዲናን ሁላችንም እንደምናውቃቸው፣ በሀገራችን የመማር ማስተማር እና የፖለቲካ ምህዳር እንደ አስተማሪም እንደ አማራሪም በመሆን ከፍተኛ ሚና የተጫወቱና አንቱታን ያተረፉ የሀገራችን ዜጋ ናቸው።  አንደበተ ርቱ ባይባሉም መናገር የፈለጉትን ነገር ከመናገር ወደኋላ የማይሉ፣ ንግግራቸው ግልፅ እና ግልብ ከሚባል ተርታ ይመደባል ባይ ነኝ። እሳቸው ተናግረው አልያም ተከራክረው ፈገግ ያላልኩበት አጋጣሚ ትዝ አይለኝም። ከሰሞኑን የመታሰራቸውን ነገር በሰማሁ ወቅት፣ አንደ ወዳጄ አቀልድ ማህደሩ ይሁን አዚዓ ማህደር እነወጃ፣ አሉ ብሎ ካካፈለኝ ፈገግ የምታሰኝ ንግግራቸውን ላካፍላቹ ወደድኩ። ነገሩ የሆነው ፓርላማ ሳሉ ነው አሉ። የወቅቱ አፈጉባኤ ደግሞ ክቡር አቶ ተሸመ ቶጋ ነበሩ። አናም የመናገር እድሉ ሲደርሳቸው አቶ ተሾመ፣ ባላቸው ማይኩን የመዝጋትና የመክፈት ስልጣን፣ ቀጥል ብለዉት ደር መራራን እንዲናገሩ ፈቀዱላቸው። እናሎ ታድያ ወቅቱ የፓርላማው አመታዊ ሪፖርት በጠቅላይ ሚንስትሩ የሚቀርብበት ነበር፣ እንደሚታወቀው ዶር መረራ ቡዙን ግዜ ፓርላማ ላይ የማይቀሩበት አጋጣሚ ይህ እንደሆነ ይታወሳል። ይህንንም አጋጣሚ በመጠቀም (ቢቆራረጥም) ሚዲያውን በአግባቡ ይጠቀማሉ። ዶር መረራ ጀመሩ ፦ "ሲለ ተሰጠኝ እድል ባመሰጊን፣ ‘ፉት ሲሏት ጭልጥ’ እንደሚለው ተረት ቲሆናለች እና የተሰጠን ሰዐት ኢሀዴግ…" ብለው ሳይጨርሱ፣ አፈጉናኤው እላያቸው ላይ ማይኩን ጥርቅም አድርጉት። አፈ ጉባኤው:– "ደ/ር መረራ ሌላ ሌላውን ይተውና አጊባብነት የለው ጥያቄ ያቅርቡ፣ ጥያቄዎት ወይም አስታየቶ ክብር ሚኒስትሩ ባቀረቡት ሪፖርት ላይ ብቻ ይሁን፣ ከተሰጦት ሰዓት 5 ደቂቃ ብቻ ይቀሮታል" ቁጣን ባለው ለዛ ብለው  እንዳበቁ...

የድንቅነሽ/ሉሲ በደህና የመመለሷ ነገር . . .

ዛሬ ድንገት ኢቲቪ ተከፍቶ ዜና ሠማሁኝ እና ከዜናው አንዱ ትኩረቴን ሳብ አድርጎት ጆሮዬን ቀልቤን አቅሌን ሙሉ ለሙሉ ለኢቲቪ ሰጠሁ፡፡ ታድያሎ ያልኳችሁ ዜና እናንተም የሰማችሁት ያ ስለ ድንቅነሽ /ሉሲ/ ከ5 ዓመት ቆይታ ቡሀላ ከወደ አሜሪካን ሀገር ተመለሰች የሚለው ነበር፡፡ ገና የዜናው ርዕስ እንደሰማሁኝ ነበር፤ እንኳን በደህና ሄደሽ ባልልም፤ እንኳን ደህና መጣሽ ማለቴ ግድ ነበር፤   እናም አልኩኝ፡፡ ሙሉ የዜናውን ሀተታ እና የምስል ቅንብር ስመለከት፤ለርክክቡም አሜሪካዊ እና ታዋቂ ብሎም አዋቂ የኢትዮጰያዊ ተመራማሪዎች ከአሜሪካን ድረስ እዚህ መገኘታቸውን ሠማሁ፡፡ ከዛማ እንኳን በደህና ተመለስሽ ያልኩት አባባል ግልፅነት እና ተጠያቂነት የጎደለው ደብዛዛ ምስክርነት መስሎ ታየኝ፤ ጥርጣሬም ወረረኝ፡፡ ለምን እና እንዴት ካላችሁ. . . . . የ እኛ ምሁራን ሉሲን ገቢ ያደረጉበት የማረጋገጫ መለኪያ ተጠቀምን ያሉት ስልት እንደ ስለት አሳቀቀኝ፡፡ ፕሮፌሰሩ ቃል ሲሰጡ፤ “እያንዳንዷን አጥንት መዝነን፣ ለክተን ነው የተቀበልነው::” በዜናው ላይ የቀረበው የ ርክክብ ቪዲዮ ላይ እንዳየነው፤  እና መገለጫችን የሆነውን የሉሲን አፅም ለዛውም ለ5 ዓመት ያህል ሠው ቤት ቆይቶ እንደሚመለስ ብርቅዬ ቁስ ሳይሆን እንደ አሞሌ ሲቀባበሉ መመልከቴ አስገርሞኛል፡፡ በተለይ በተለይ የእኛው ምሁራን ይህችን በስንት ምርምር የእድሜ ጠገብነቷን ሚስጢር በዓለም አቀፍ ደረጃ ለመለየት ብዙ ምርምር የተደረገላትን በክብደት እና ቁመት በመለካት ማረጋገጥ ችለናል ማለታቸው አግራሞት ፈጥሮብኛል፡፡ እኔ የምለው እንደው ደረጃ መዳቢዎች ባለስልጣን እራሱ ዘይትን ከውጪ ለማስገባት ምን ያህል የላብራቶሪ ፍተሸ እናደሚያካሂድ ባለፈው ዘይት እንትን ያ...