Skip to main content

ለዳግመኛ ፍቅር!


የባጡን የቆጡን ማህላ እየማልኩልሽ
ልሰቀል ነው ልሞት ብዬ ጎተጎትኩሽ
ልብሽን ሸርሽሬ የእኔ የብቻዬ ትሆኝ ዘንድ አረግኩሽ፤
የት ይደርሳል ሲባል አይን ውስጥ ገባሁና
እንደ በሬው ሆንኩኝ ቄራ ታየሁና፡፡

አንቺ እያለምሽኝ ያገባኛል ብለሽ ሳላገባሽ ቀረሁ
መጥፎሽን አግዝፌ ቀስ ብዬ ሸሸሁ
ጥሩሽን ሸሽጌ ገላ ጠረንሽን አሽቼ ብጠግበው፤
እውነት ለመናገር
ዛሬ ላይ ቁጭብዬ ትላንትን ስለካ
‘በእጅ-ያለ-ወርቅ …..’ እንዳሉት፣ ውስጤ ይፀፅታል በሚዘው አይረካ፡፡

እስካሁን ብቆይም፣ ደብቄሽ ስሜቴን፣ አልሸነፍ ብዬ
ሲያይሽ ልቤ እንደ አዲስ፣ ወጥተሽ ከጉያዬ፤
እንዳልሆነ ምንም፣ አንቺን ሲመለከት
የሚያደርገው ነገር፣ እንደሆነ ውሸት፤
በእናቴ ምላለው፣ እየታገለው እንጂ፣ የልቡን መፀፀት
ፊቴ-ይናፍቀዋል፣ ፊቴ ያስፈልገዋል፣ የያኔው ፈገግታ የያን ግዜው ስሜት፡፡

እውነት የኔ ፍቅር፣ እውነት ለመናገር
ያዛኔን ሽርሽር የየያኔ ገላሽን፣ ለሊት እንኳ ሳይቀር፤
ቀንማ ምንላድርግ፣ አምረሽ እያየሁሽ ፈርቼ ተዋለሁ
ለሊት ማን ከልክሎኝ፣ እኮመኩማለሁ
የያኔው አልበሜን፣ ላይሽ ከፎቶዬ፣ እንደከሰረ ዓረብ አገላብጣለሁ፡፡

ዓይኔን በጨው ባጥብም፣ ባይሠማኝ ዩሉኝታ
እድል ስጪኝ ውዴ፣ እስኪ ለአንድ ላፍታ፤
ልቤ ልብ ገዝቶ፣ ለመመራት መቷል፣ የይቅርታን ቦታ
አጢኚው ደጋግመሽ፣ ይህን አቤቱታ፡፡

ገንፍሎ ሲያገረሽ ፣ ሆንሽና ስራዬ
መጣሁ ያንቺ ጠላት፣ ሁለቴ ልማረክ፣ እጅ ወደላይ ብዬ
ነጠላ አዘቅዝቄ፣ ቅንድቤን ላጭቼ፣ እያለቃቀስኩኝ ውስጥሽን ገድዬ፤
ከደሙ እንደነፃ፣ ለቅሶው ላይ ያቆመኝ
ምክንያቱን እወቂ፣ በዳግመ-መውደድሽ፣በዳግመኛው-ፍቅርሽ፣ አቅሌን ስላጣሁኝ፤
እንደ እጣ ወጥቼ፣ እጅሽ ገብቻለሁ
 ያረግሽኝን አድርጊኝ ፈቅጄልሻለሁ፤
ስትፈልጊ ብይኝ፣ አልያም እንዳሻሽ፣ ዘልዝለሽ ስቀይኝ
ግን ከልብሽ ጓዲያ፣ ከወጠርሽው ገመድ፣ ዘርግተሸ አድርቂኝ፤
ይቅር ብለሽ በይኝ!!

© በአኒቲ/by Aniti
ጥቅምት፣ 2005/Nov, 2012

Comments

Popular posts from this blog

ሳላሀዲን ሰዓድ ካዋራኝ የተገለበጠ ኢንተርቪው

Invisible journalist asking question through Magnetic Force of the mind First Audition የእምነት ነፃነት መፅሄት የመጀመሪያው እትም በሆነው ቅፅ ፻ የእንግዳችን ፕሮግራም አምድ ላይ ተጋባዥ ያደረግነው የጭንቅ ቀን ደራሹ የብሄራዊ ቡድናችን አጥቂ ከሆነው ሳላሀዲን ሰዒድ ጋር ያደረግነውን አጭር ቆይታ እነሆ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡ የእምነት ነፃነት መፅሄት ፡ ሳላሀዲን መቼም በዚህ አጭር ግዜ ውስጥ (ልምምድ ላይ እንደመሆንህ መጠን) ለቃለ ምልልሱ ፍቃደኛ ሆነህ ስለመጣህ እያመሰገንን በቅድሚያ በአንባቢዎቻችን ስም እንኳን በደህና መጣህ ለማለት እንወዳለን፡፡ ሳላሀዲን ፡ እንኳን ደህና ቆያችሁኝ፣ የመጀመርያ እንግዳም ስላደረጋችሁኝ አመሰግናለሁ፡፡ ጥያቄ ፡ ሙስሊም እንደመሆንህ መጠን የመጅሊስ ምርጫ በቀበሌ መባሉን እንዴት ነበር ያየህው? ሳላሀዲን ፡ በግልምጫ፡፡ ጥያቄ ፡ ለምን? ሳላሀዲን፡ ምክንያቱም ድርጊቱ በመረብ ኳስ ሜዳ ላይ ጎል ተክሎ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያን የመጫወት ያህል ነው፡፡ ጥያቄ፡ የመንግስት አካላት ምርጫው በቀበሌ መሆኑ ህገመንግስቱን አይፃረንም ባዮች ናቸው አንተ ምን ትላለህ? ሳላሀዲን፡ እግር ኳስ ተጫዋች ስለሆንኩ የመረዳት አቅም የለውም በእግር ማሰብ አይደለም እንደማትለኝ እያመንኩ፡፡ ይህ ቀላል ጥያቄ ነው በሚቀጥለው ምርጫ 2007 የመንግስት ተወካይን ለመምረጥ የሀገሪቱ ህዝብ በመስጊድ እና በቤተክርስታን ማከናወን እንደሚችል ቃል ከገቡና በምርጫ ቦርድ ወይም በፓርላማው እንደ አንድ ፖሊሲ ካፀደቁት ምንም ችግር የለውም ባይ ነኝ፡፡ ጥያቄ፡ በሌላ መንገድ እምነት እና ፖለቲካን (ሰርግና ሞት አንድ ነው ጨፍር ምንድነው) እንደሚለው የ...

The Historic Chaltu Speeks Out

Let me paint you the picture of what happened in ATL yesterday. Me and Riyad S abona walking, minding our own business and we see an anti-Jawar protest happening 200 yards away from the meeting entrance. The police directed us to walk in closer to the side of the protest to avoid obstructing traffic.  So we saw their flags and I decided to take out my Oromo flag and walk.  First, it was just the slurs, calling me Galla. Then it was the spit, in front and behind me and then one made it with the perfect aim to hit my cheek. I continued to walk with my head high with the utmost respect until one 'balance' thought it would be okay to reach over and snatch my flag. He thought he got the flag, but I killed that dream, but as soon as he reached again and grabbed my hijab, I turned around and his face hit the back of my hand (like how words can change everything?). Lol, I actually slapped the hell out of him. When I looked back they were grabbing on Riyad's trad...

ከዶ/ር መረራ አስለቃሽ ጭስ አንዷ

ዶር መረራ ጉዲናን ሁላችንም እንደምናውቃቸው፣ በሀገራችን የመማር ማስተማር እና የፖለቲካ ምህዳር እንደ አስተማሪም እንደ አማራሪም በመሆን ከፍተኛ ሚና የተጫወቱና አንቱታን ያተረፉ የሀገራችን ዜጋ ናቸው።  አንደበተ ርቱ ባይባሉም መናገር የፈለጉትን ነገር ከመናገር ወደኋላ የማይሉ፣ ንግግራቸው ግልፅ እና ግልብ ከሚባል ተርታ ይመደባል ባይ ነኝ። እሳቸው ተናግረው አልያም ተከራክረው ፈገግ ያላልኩበት አጋጣሚ ትዝ አይለኝም። ከሰሞኑን የመታሰራቸውን ነገር በሰማሁ ወቅት፣ አንደ ወዳጄ አቀልድ ማህደሩ ይሁን አዚዓ ማህደር እነወጃ፣ አሉ ብሎ ካካፈለኝ ፈገግ የምታሰኝ ንግግራቸውን ላካፍላቹ ወደድኩ። ነገሩ የሆነው ፓርላማ ሳሉ ነው አሉ። የወቅቱ አፈጉባኤ ደግሞ ክቡር አቶ ተሸመ ቶጋ ነበሩ። አናም የመናገር እድሉ ሲደርሳቸው አቶ ተሾመ፣ ባላቸው ማይኩን የመዝጋትና የመክፈት ስልጣን፣ ቀጥል ብለዉት ደር መራራን እንዲናገሩ ፈቀዱላቸው። እናሎ ታድያ ወቅቱ የፓርላማው አመታዊ ሪፖርት በጠቅላይ ሚንስትሩ የሚቀርብበት ነበር፣ እንደሚታወቀው ዶር መረራ ቡዙን ግዜ ፓርላማ ላይ የማይቀሩበት አጋጣሚ ይህ እንደሆነ ይታወሳል። ይህንንም አጋጣሚ በመጠቀም (ቢቆራረጥም) ሚዲያውን በአግባቡ ይጠቀማሉ። ዶር መረራ ጀመሩ ፦ "ሲለ ተሰጠኝ እድል ባመሰጊን፣ ‘ፉት ሲሏት ጭልጥ’ እንደሚለው ተረት ቲሆናለች እና የተሰጠን ሰዐት ኢሀዴግ…" ብለው ሳይጨርሱ፣ አፈጉናኤው እላያቸው ላይ ማይኩን ጥርቅም አድርጉት። አፈ ጉባኤው:– "ደ/ር መረራ ሌላ ሌላውን ይተውና አጊባብነት የለው ጥያቄ ያቅርቡ፣ ጥያቄዎት ወይም አስታየቶ ክብር ሚኒስትሩ ባቀረቡት ሪፖርት ላይ ብቻ ይሁን፣ ከተሰጦት ሰዓት 5 ደቂቃ ብቻ ይቀሮታል" ቁጣን ባለው ለዛ ብለው  እንዳበቁ...