የድሮው ተማሪ የያኔ ጠብሼ
ኦልድ ካሪኩለም በፍቅሬ አንግሼ፤
ለስሙ ተምራ ምሁር ተብላለች
በዚያ የዋህ ዘመን ሥራ የተቀጠረች፤
እናላእሁ ታድያ አሁን በቀደም ለት
ሥራ ቀይር ብላ ማንበብ ቢያስፈልጋት፤
በአንድ ቢሮ ፊርማ ጫማዋን ማንጠልጠል መስቀል
ቢደብራት
መዋሉን ጀመረች ቀኑን ሙሉ ስትዞር እንጀራ ሲያዞራት፤
ለሷ የሚመቻት የምታውቀው ቢኖር
የአዲስ ዘመን እትም አልያም ሪፖርተር፤
ethio-jobs ብል አታርፈው ነገር
ተሰታ ትውላለች ከአራትኪሎ ደጃፍ እስከ ታች ለገሀር
ለብይ ጫወታ ሲንፏቀቅ እንደዋለ ጨቅላ ህፃን በሠፈር
እማስታወቂያ ደጅ ከጋዜጦች መንደር፤
ሼም ደግሞ የላትም ሁሌም ትዝታለች
ትምህርት ድሮ ቀረ በኛ ግዜ እያለች፡፡
እውነት ለመናገር
የትምህርቱ ጥራት የያኔ ይሻል ነበር፤
ቅሉ ምን ያደርጋል ታበሳጨኛለች
IT አታርፍም ታሳዝነኛለች፤
Technology ነገር ያጥወለውላታል
Computer ስታይ ነስር ይነስራታል፤
እንኳን እና facebook አንድ email የሌላት
ግራ ነው ሚገባኝ ዘወትር ሳስባት፤
እንደ እኔ እንዳትሆኑ ህይወቴን ያያቹ
እናም ጨምሩበት በያዛቹት መስፈርት እንደዚህ ብላቹ፤
ለም ት ጠብሱት ጥብስ ለነጌ አጋራቹ
ለሚስት ብቻ ሳይሆን ብሎም ለባላቹ
የማግብያ ፈተና Computer Literate መስፈሪያ
ይሁናቹ
እጅጉን እንዲያምር እንዲዘልቅ ፍቅራቹ፡፡
Aniti
Nov, 2012
For the girl lol
Aniti
Nov, 2012
For the girl lol

Comments
Post a Comment