በተጠናው ጥናት፤
ባረግነው ሙከራ
ሼም የለውም ሣይንስ፤
እንደው ጉድ አይፈራ
እንስማው አንስማው?
ከእግር ከፍ በሉ፣ ሲለን ለሠገራ፡፡
ለማረጋገጫ፣
Lab እንኳን ባይኖረን
መቀበል አይከፋም፣
ሳይንስ ካለችሁን እንቀበላለን፡፡
ዳሩ ግን …
ኮንዶሚንየሙ፤ የየቤቱ
ጥበት ስለሚያስጨንቀን
የእግር መስቀያ፣
ተጨማሪ ወጪ፣ እንቃወማለን፤
ለማጣጣል ሳይሆን፣
ሳይንስ ስለሆነ፤ ሳይንሱ ልክ ነው
ለኛ ለሀገሬው፤
መፍቴሄውም ቀላል ነው
ሲንኩን ዞር አድርጎ፣
ወደ ቀድሞ ጉርጓድ፤ ቶሎ መመለስ ነው፡፡
ግን ግን …
ወጪን ብናስቀርም፣
ይህንን ተግብረን
የማይካድው ሀቅ፣
ሀገራዊ ችግር፣ አንዲት ጉድፍ አለን
አልሞ መተኮስ፣
አነጣትሮ ማራት፣ ለጉድ ነው ሚያቅተን፡፡
በተለይ በተለይ
…
ካምፓስ ዩንቨርሲቲ፣ ሽንት ቤት ፍለጋ፣ ድንገት ጎራ ካልን
የኛ ሠው እንዲ ያራል? ብለን ባለማመን፣ እንደመማልን
ቀበሌ ሲለጠፍ፣
ሲባል ከአር ነፃ፤ ደግመን እንጠይቅ፤ እና ምን ተሻለን?
የተማረው ምሁር፣
አልሞ ካላራ
ከቀበሌ እንዲማር፣
ምን ስራ ይሠራ???
ለዚህም አምስት
ለ አንድ እንዳትሉኝ ብቻ፡፡
© Aniti
to read more about this new development go to
http://www.lacocinaalternativa.com/2012/10/03/como-defecar-correctamente/

Comments
Post a Comment