Skip to main content

ቂጥ የሌለው ደሞዝ!

የአባቴን ደሞዝ፣ ድሮ ድሮ ሳውቀው
ለሙሉ ቤት ወጪ፤ በወር ሲቆጥበው
ከባልደረባው ጋር፣ እቁብ እየጣለው
ቤት ሠራ፣ እቃ ገዛ፣ ኣረ ምኑ ቀረው፡፡
እኔም ሥራ ይዤ፤ ሆንኩና ተከፋይ
ህዝብ የሚያገለግል፣ የአባቱ ተከታይ፤
ምን ያደርጋል አሁን፣ ነገር ተቀይሯል
በሥም እንጂ ደሞዝ፣ ሲወሰድ ይከሳል
እንኳን ለቁጠባ፣ መች ለጉርስ ይበቃል!
የኮስት ሼሪንጉ፣ የግብሩ ብዛት
የዓባል የዓባይ፣ የመዋጮው ብዛት፣
ለቤተሠብ ጣጣ፣ ያለበት ትኩሳት
የዘይት የስኳር፣ የክራይ ቤት ንረት
ከሻይ ማኪያቶ፣ የሚቆረጠው ቫት
የጂንስ መወደድ፣ የሠልባጅም ልብስ መጥፋት፡፡
ኣረ ምኑን ትቼ፣ ምኑንስ ላነሳው
ብቻ ተቆራርጦ፣ ኪሴ ስለገባው
ይናገር ፔሮሌ፣ ጠይቁት ዋሌቴን፣ አሱ ነው የነጣው፡፡
እንኳን እንዳባቴ፣ ትዳር አስመስርቶ
ጎጆን አስቀልሶ፣ ቤት ሊሞላ ቀርቶ
አይደለም ለእቁብ፣ መች ዋለቴስ ገብቶ፣
አረ መች ሊገባ፣ ገብቶስ ምን ፈየደኝ
እንደ ድሮው ሆኖ፣ መች ተቀመጠልኝ፡፡
ለነገሩ
እሱም እውነት አለው፣ ምን ማድረግ ይችላል
ከሄደበት ልከው፣ ሳይደርስ ይጠሩታል
ቂጥ የሌለው ደሞዝ፣ መቼ ይቀመጣል፡፡

December 21/12/12
መታሠቢያነቱ ለደሞዝተኛ
© አኒቲ


Comments

Popular posts from this blog

ሳላሀዲን ሰዓድ ካዋራኝ የተገለበጠ ኢንተርቪው

Invisible journalist asking question through Magnetic Force of the mind First Audition የእምነት ነፃነት መፅሄት የመጀመሪያው እትም በሆነው ቅፅ ፻ የእንግዳችን ፕሮግራም አምድ ላይ ተጋባዥ ያደረግነው የጭንቅ ቀን ደራሹ የብሄራዊ ቡድናችን አጥቂ ከሆነው ሳላሀዲን ሰዒድ ጋር ያደረግነውን አጭር ቆይታ እነሆ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡ የእምነት ነፃነት መፅሄት ፡ ሳላሀዲን መቼም በዚህ አጭር ግዜ ውስጥ (ልምምድ ላይ እንደመሆንህ መጠን) ለቃለ ምልልሱ ፍቃደኛ ሆነህ ስለመጣህ እያመሰገንን በቅድሚያ በአንባቢዎቻችን ስም እንኳን በደህና መጣህ ለማለት እንወዳለን፡፡ ሳላሀዲን ፡ እንኳን ደህና ቆያችሁኝ፣ የመጀመርያ እንግዳም ስላደረጋችሁኝ አመሰግናለሁ፡፡ ጥያቄ ፡ ሙስሊም እንደመሆንህ መጠን የመጅሊስ ምርጫ በቀበሌ መባሉን እንዴት ነበር ያየህው? ሳላሀዲን ፡ በግልምጫ፡፡ ጥያቄ ፡ ለምን? ሳላሀዲን፡ ምክንያቱም ድርጊቱ በመረብ ኳስ ሜዳ ላይ ጎል ተክሎ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያን የመጫወት ያህል ነው፡፡ ጥያቄ፡ የመንግስት አካላት ምርጫው በቀበሌ መሆኑ ህገመንግስቱን አይፃረንም ባዮች ናቸው አንተ ምን ትላለህ? ሳላሀዲን፡ እግር ኳስ ተጫዋች ስለሆንኩ የመረዳት አቅም የለውም በእግር ማሰብ አይደለም እንደማትለኝ እያመንኩ፡፡ ይህ ቀላል ጥያቄ ነው በሚቀጥለው ምርጫ 2007 የመንግስት ተወካይን ለመምረጥ የሀገሪቱ ህዝብ በመስጊድ እና በቤተክርስታን ማከናወን እንደሚችል ቃል ከገቡና በምርጫ ቦርድ ወይም በፓርላማው እንደ አንድ ፖሊሲ ካፀደቁት ምንም ችግር የለውም ባይ ነኝ፡፡ ጥያቄ፡ በሌላ መንገድ እምነት እና ፖለቲካን (ሰርግና ሞት አንድ ነው ጨፍር ምንድነው) እንደሚለው የ...

The Historic Chaltu Speeks Out

Let me paint you the picture of what happened in ATL yesterday. Me and Riyad S abona walking, minding our own business and we see an anti-Jawar protest happening 200 yards away from the meeting entrance. The police directed us to walk in closer to the side of the protest to avoid obstructing traffic.  So we saw their flags and I decided to take out my Oromo flag and walk.  First, it was just the slurs, calling me Galla. Then it was the spit, in front and behind me and then one made it with the perfect aim to hit my cheek. I continued to walk with my head high with the utmost respect until one 'balance' thought it would be okay to reach over and snatch my flag. He thought he got the flag, but I killed that dream, but as soon as he reached again and grabbed my hijab, I turned around and his face hit the back of my hand (like how words can change everything?). Lol, I actually slapped the hell out of him. When I looked back they were grabbing on Riyad's trad...

ከዶ/ር መረራ አስለቃሽ ጭስ አንዷ

ዶር መረራ ጉዲናን ሁላችንም እንደምናውቃቸው፣ በሀገራችን የመማር ማስተማር እና የፖለቲካ ምህዳር እንደ አስተማሪም እንደ አማራሪም በመሆን ከፍተኛ ሚና የተጫወቱና አንቱታን ያተረፉ የሀገራችን ዜጋ ናቸው።  አንደበተ ርቱ ባይባሉም መናገር የፈለጉትን ነገር ከመናገር ወደኋላ የማይሉ፣ ንግግራቸው ግልፅ እና ግልብ ከሚባል ተርታ ይመደባል ባይ ነኝ። እሳቸው ተናግረው አልያም ተከራክረው ፈገግ ያላልኩበት አጋጣሚ ትዝ አይለኝም። ከሰሞኑን የመታሰራቸውን ነገር በሰማሁ ወቅት፣ አንደ ወዳጄ አቀልድ ማህደሩ ይሁን አዚዓ ማህደር እነወጃ፣ አሉ ብሎ ካካፈለኝ ፈገግ የምታሰኝ ንግግራቸውን ላካፍላቹ ወደድኩ። ነገሩ የሆነው ፓርላማ ሳሉ ነው አሉ። የወቅቱ አፈጉባኤ ደግሞ ክቡር አቶ ተሸመ ቶጋ ነበሩ። አናም የመናገር እድሉ ሲደርሳቸው አቶ ተሾመ፣ ባላቸው ማይኩን የመዝጋትና የመክፈት ስልጣን፣ ቀጥል ብለዉት ደር መራራን እንዲናገሩ ፈቀዱላቸው። እናሎ ታድያ ወቅቱ የፓርላማው አመታዊ ሪፖርት በጠቅላይ ሚንስትሩ የሚቀርብበት ነበር፣ እንደሚታወቀው ዶር መረራ ቡዙን ግዜ ፓርላማ ላይ የማይቀሩበት አጋጣሚ ይህ እንደሆነ ይታወሳል። ይህንንም አጋጣሚ በመጠቀም (ቢቆራረጥም) ሚዲያውን በአግባቡ ይጠቀማሉ። ዶር መረራ ጀመሩ ፦ "ሲለ ተሰጠኝ እድል ባመሰጊን፣ ‘ፉት ሲሏት ጭልጥ’ እንደሚለው ተረት ቲሆናለች እና የተሰጠን ሰዐት ኢሀዴግ…" ብለው ሳይጨርሱ፣ አፈጉናኤው እላያቸው ላይ ማይኩን ጥርቅም አድርጉት። አፈ ጉባኤው:– "ደ/ር መረራ ሌላ ሌላውን ይተውና አጊባብነት የለው ጥያቄ ያቅርቡ፣ ጥያቄዎት ወይም አስታየቶ ክብር ሚኒስትሩ ባቀረቡት ሪፖርት ላይ ብቻ ይሁን፣ ከተሰጦት ሰዓት 5 ደቂቃ ብቻ ይቀሮታል" ቁጣን ባለው ለዛ ብለው  እንዳበቁ...